???? በምርጫው በህዝባዊ ስፍራ በመተኛት የሚታወቁት እና በቅፅል ስማቸው “እንቅልፋሙ ጆሴፍ” የሚባሉት አሸንፈዋል
የቀድሞዉ እግርኳስ ተጨዋች እና ብቸኛዉ አፍሪካዊ የባሎን ዶር አሸናፊ ጆርጅ ዊሃ በላይቤሪያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ መሸነፉቸው መነገሩ ይታወሳል።
ዊሃ ከዚህ ቀደም እ.ኤ.አ በ 2017 አመት በምርጫ አሸንፏቸዉ በነበሩት የ 78 አመቱ የቀድሞዉ ም/ል ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ቦአካይ መሸነፉቸው በምርጫ ኮሚሽኑ ተረጋግጧል።በጠባብ ልዩነት የተሸነፉት ዌሃ ሽንፈታቸውን አምነው በመቀበል ስልጣን እንደሚለቁ ተናግረዋል።በሁለተኛው ዙር ምርጫ ቦአካይ 50.9 በመቶ የመራጮችን ድምፅ ሲያገኙ ዊሃን በአንጻሩ 49.1 መራጮች በፕሬዚዳንትነት እንዲመራቸዉ ድምፅ ሰጥተዋቸው ነበር።
ዌሃ የመራጮችን ድምፅ ለማጣታቸው በድህነት ፣ ስራ አጥነት ፣ የምግብ ደህንነት እና የኤሌክትሪክ ሀይል ተደራሽነት ላይ በሚገባዉ ልክ አልሰሩም በሚል መሆኑን የሮይተርስ ዘገባ ያመላክታል። በተጨማሪም ዌሃ ወደ ስልጣኑ ሲመጡ የገቧቸውን ቃል አልፈጸሙም በሚል ይተቻሉ።በሁለቱ ፕሬዚዳንታዊ እጩዎች መካከል ከዚህ ቀደም በተካሄደዉ ምርጫ ከ 50 በመቶ በላይ ድምፅ ማግኘት ተስኗቸዉ ዳግመኛ በሁለተኛ ዙር በተካሄደዉ ምርጫ ነዉ የቀድሞዉ ም/ል ፕሬዚዳንት ድል የቀናቸዉ።
ዌሃ ለአዲሱ ፕሬዚዳንት የእንኳን ደስ አለህ መልዕክት በብሔራዊ ሬዲዮ ጣቢያ ላይ አስተላልፈዋል ተብሏል። በርካታ ላይቤሪያዊያንም አዲሱ ፕሬዚዳንት የስራ እድል ፈጠራ ላይ እንደሚሰሩ ተስፋ አድርገዋል።በላይቤሪያ 250 ሺ ሰዎችን የገደለው የእርስ በርስ ጦርነት ካበቃ በኋላ ይህ አራተኛው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ነው። በአፍሪካ የመጀመሪያዋ ሴት መሪ ለሆነችው ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ በምክትል ፕሬዝዳንትነት ያገለገሉ ቦአካይ፣ ጥሩ አፈጻጸም ካላቸው አራቱ እጩዎች የሶስቱን እውቅና ማግኘታቸውን ለአሸናፊነታቸው አስተዋጾ አድርጓል።
በምርጫ ዘመቻቸው በግብርና እና በመሰረተ ልማት ላይ ኢንቨስት ማድረግ ላይ ትኩረት አድርገዋል። ዊህ ስለ ትምህርት ማሻሻል እና ስራ አጥነትን ለመቅረፍ እንደሚሰሩ ቃል ገብተው ነበግ። ዊሃ ከዚህ ቀደም በምርጫ እንዲያሸንፉ ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ኮከብነት በወጣቶች ዘንድ ያለውን ተወዳጅነት እንደረዳቸው እና ለመራጮችም ሙስናን ለመግታት በገቡት ቃል መሰረት ተማርከው ነበር ይላሉ ተንታኞች።ቦአካይ ጆሴፍ በህዝባዊ ስፍራ እና በስብሰባ ላይ እንቅልፍ ስለሚጥላቸው እንቅልፋሙ ጆሴፍ የሚል ቅፅል ስም አላቸው።
በምህረት ታደሰ