መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 12፤2016 –በኮሎራዶ የፕላስቲክ የቀዶ ህክምና ሐኪም ለአንዲት ታዳጊ የጡት ማስተለቅ ህክምና ከሰጠ በኃላ ህይወቷ በማለፉ ጥፈተኛ ተባለ

የኮሎራዶ ፕላስቲክ የቀዶ ህክምና ሐኪም የጡቷን መጠን ለማስተለቅ ለመጣች ታዳጊ አስፈላጊውን የማደንዘዣ መጠን ሰባት እጥፍ ከፍ በማድረጋቸው ለመተንፈስ መቸገሯ እና እርዳታ ለማግኘት አምስት ሰአት ያስጠበቋት በመሆኑ ጥፋተኛ ተብለዋል።

የ54 አመቱ ዶ/ር ጂኦፍሪ ኪም በሰኔ ወር ላይ ሰራተኞቻቸው ወደ 911 የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት እንዳይደውሉ በመከልከላቸው በግዴለሽነት ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል። የአራፓሆ ካውንቲ አውራጃ ፍርድ ቤት ዳኞች ዶክተሩን ከቀረበበት ከባድ ክስ በቸልተኝነት ግድያ ከሚለው በነጻ አሰናብተዋል። ሆኖም ለሁለት አመታት በገደብ እና ዶ/ር ኪም 70,000 የአሜሪካ ዶላር እንዲከፍል ተወስኗል።

በተጨማሪም ለ120 ሰአታት የማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሰጥ ውሳኔ ተላልፏል።የኮሎራዶ ሕክምና ቦርድ የኪም ፈቃድን ላልተወሰነ ጊዜ አግዶታል።የ18 ዓመቷ ሟች ንጉየን የምትባል ሲሆን ጡት ለማስተለቅ ለሚረዳው ህክምና 6,000 ዶላር ወጪ ማድረጓን ወላጅ እናቷ ልጅዋ በህይወት እያለች ለሲቢኤስ ኒውስ ተናግራ ነበር። ለ14 ወራት በኮማ ውስጥ ከቆያች በኋላ ንጉየን በ19 ዓመቷ በሆስፒስ እንክብካቤ ውስጥ እያለች ህይወቷ አልፏል።

ከኪም ጋር በኮሎራዶ የውበት እና ፕላስቲክ ቀዶ ህክምና የሚሰሩ ነርሶች ዋቢ በማድረግ በተሰጠው መረጃ የንጉየን ጡት በማሳደግ ሂደት ላይ ልቧ መምታቱን ሲያቆም ለእርዳታ ለመደወል እንደሚፈልጉ ቢናገሩም ዶ/ር ኪም 911 መደወል እንደማይችሉ ማስጠንቀቃቸውን አቃቤ ህግ ኬልሲ ቲፕስ በችሎቱ የመክፈቻ ንግግሯ ላይ ገልጻለች። ዶ/ር ኪም ለሟች እናት ልጇ ለህክምናው ገብታ ሰአታት እያለፉ ሲሄዱ ደህና መሆኗን ደጋግሞ ማረጋገጫ ሰጥቷል። በመጨረሻም ሴትየዋ ልጇን ለማየት ከጠየቀች በኋላ የአደጋ ጊዜ አገልግሎት ተጠርቷል።

የዶ/ር ኪም የጠበቆች ቡድን የአደጋ ጊዜ አገልግሎት የዘገዩት ጊዜ ምንም ይሁን ምን፣ የተሰጠው የማደንዠዣ መጠን ገዳይ እንደሚሆን በፍርድ ቤቱ ተከራክረዋል።በዚህም የተነሳ በግሪንዉዉድ፣ ኮሎራዶ፣ ክሊኒክ የቀድሞ ሰመመን ሰጪ የነበረው ሬክስ ሜከር በወንጀሉ በቸልተኝነት ግድያ እና ግድየለሽነት ክስ ቀርቦበታል። ሜከር ላይ የቀረበው ክስ ውድቅ ቢሆንም በዶ/ር ኪም ላይ ግን መመስከሩን ቀጥሏል። ወደ ሆስፒታል እንድንልክላት ነግሬው ነበር ሲል ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።

የሟች ንጉየን እናት ሊን ፋም የልጇን ህልፈት በተመለከተ እና የዶ/ር ኪም ቅጣት ላይ አሁንም እየተከታተለች መሆኑ ገልጻለች። ዶ/ር ኪም ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጪ ለተፈጠረው ጉዳት ለኑጉየን ቤተሰብ 1 ሚሊየን ዶላር እንደከፈለ ተዘግቧል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *