መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 12፤2016 – የጋና አንድ የፓርላማ አባል ደካማ የስራ አፈፃፀም ያላቸውን የሀገሪቱን ምክትል ፕሬዝዳንት ከሃሪ ማጓየር ጋር በማነፃፀራቸው ተጫዋቹን ይቅርታ ጠይቁ

???? ማጓየር አሁን ተሻሽሏል ሲሉ ተናግረዋል

የጋና የፓርላማ አባል እንግሊዛዊውን እግር ኳስ ተጫዋች ሃሪ ማጓየርን ከሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ጋር በማነፃፀር ደካማ አፈፃፀም እንዳላቸው በመግለጽ ባደረጉት ንግግር ተጫዋቹን ይቅርታ ጠይቀዋል። የፓርላማ አባል ባለፈው አመት ምክትል ፕሬዝዳንቱን ማሃሙዱ ባውሚያን በጋና ደካማ የኢኮኖሚ አፈጻጸም ላይ ተችተውታል።

በትችታቸውም በራሱ መረብ ላክ ግቦች በማስቆጠር ከሚታወቀው ማጓየር ጋር በማነፃፀር ሁለቱም ደካማ አፈጻጸም አላቸው ሲሉ ተናግረው ነበር። ነገር ግን የፓርላማ አባሉ አይዛክ አዶንጎ የማንቸስተር ዩናይትድ ተከላካይ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በብቃት እየተጫወተ ነው ብለዋል።

ባስተላለፉት የይቅርታ መልዕክት “የተከበሩ የምክር ቤቱ አፈ-ጉባዔ፣ አሁን ሃሪ ማጉየርን ይቅርታ እጠይቃለሁ። ዛሬ ላይ ሃሪ ማጉየር ያ የስህተት መንገዱን ቀይሮ የተለወጠ እግር ኳስ ተጫዋች ሆኗል” ሲሉ በበጀት ክርክር ወቅት በፓርላማው ላይ ተናግረዋል። የምክር ቤቱ አባል ምክትል ፕሬዝዳንት እና የጋና ኢኮኖሚ አስተዳደር ቡድን መሪ ባዉሚያን አፈጻጸምን ተችተዋል።

የስራ አፈፃፀማቸው ሀገሪቱን የበለጠ ዕዳ ውስጥ እንድትገባ በማድረግ ኢኮኖሚያዊ አደጋ ላይ ጥሏታል ብለዋል። ሃሪ ማጉየር አሁን ለማንቸስተር ቁልፍ ተጫዋች ነው ነገርግን የኛ ማጉዌር ወይም ምክትል ፕሬዝዳንቱ ዋንጫ በእጁ ይዞ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም አይኤምኤፍ ውስጥ እየተንከራተተ ነው ብለዋል።

ጋና በአሁኑ ጊዜ ከአንድ ትውልድ እድሜ በላይ የከፋ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ትገኛለች። ባለፈው ዓመት የዋጋ ግሽበቱ 54 በመቶ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። አሁንም ከ35 በመቶ በላይ ይገኛል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *