መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 14፤2016 – የእስራኤል እና ሃማስ ጦርነት ለአራት ቀናት የተኩስ እረፍት መደረሱን ተከትሎ የእርዳታ ድጋፍ ወደ ጋዛ እየገባ ይገኛል

የተኩስ እረፍት በሃማስ እና እስራኤል መካከል መደረሱን ተከትሎ ስልሳ የጭነት ተሽከርካሪዎች የህክምና ቁሳቁሶችን፣ ነዳጅ እና ምግብን የጫኑ ከግብፅ ወደ ጋዛ ገብተዋል። በኳታር ሸምጋይነት በተደረገው ስምምነት 13 እስራኤላውያን ታጋቾች ዛሬ ቤተሰቦቻቸውን የሚለቀቁ ሲሆን 50ዎቹ በአራት ቀናት ውስጥ ከእስር እንደሚፈቱ ይጠበቃል።

በስምምነቱ መሰረት እስራኤል 150 የፍልስጤም እስረኞችን ትፈታለች። የትንሽ መሳሪያዎች እና የሞርታር ተኩስ እንዲሁም የአየር ድብደባ የተኩስ እረፍቱ ከመደረሰ ከደቂቃዎች በፊት ለጋዛ ቅርብ በሆኑ ቦታዎች ላይ ተሰምቷል።

የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን ዛሬ ከፍልስጤም መሪዎች ጋር የተገናኙ ሲሆን ብሪታንያ በጋዛ ውስጥ ድጋፍ ለማስገባት ሁሉንም መንገዶች እየተመለከተች ነው ብለዋል። በጥቅምት 7 የሃማስ ጥቃት ተከትሎ በእስራኤል ከ1,200 በላይ ሰዎች ሲገደል 240 ያህሉ ደግሞ ታግተዋል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስራኤል በወሰደችው የአፀፋ ጥቃት በጋዛ ሃማስ የሚመራው የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ከ14,000 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ይፋ አድርጓል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *