መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 27፤2016 – የአሜሪካ ሴኔት አባል በርኒ ሳንደርስ የኔታንያሁ አስተዳድር ሰላማዊ ሰዎችን ገድሏል በሚል ድጋፍ ማድረግ የለብንም አሉ

???? ሪፐብሊካኖች ለዩክሬንን እና ለእስራኤል እርዳታ እንዲደረግ የቀረበውን ረቂቅ አገዱ

የሴኔቱ ሪፐብሊካኖች የዩክሬን የእርዳታ ድጋፍን ለማጽደቅ የነበረውን ድርድር ማስከበር ባለመቻላቸው የረቂቅ ህጉን አግደዋል። የ 110 ቢሊዮን ዶላር ጥቅል ድጋፍ ውስጥ ለዩክሬን 61 ቢሊዮን ዶላር የሚሰጥ ሲሆን እንዲሁም ለእስራኤል እና ለጋዛ ዕርዳታን ያካትታል ። ሪፐብሊካኖች ለዩክሬን የሚሰጠው ማንኛውም እርዳታ ከአሜሪካ የኢሚግሬሽን እና የጥገኝነት ማሻሻያ ጋር የተያያዘ መሆን እንዳለበት አጥብቀው እየገለጹ ይገኛል።

ዋይት ሀውስ አሜሪካ ለዩክሬን የምትሰጠው ገንዘብ በቅርቡ ሊያበቃ እንደሚችል አስጠንቅቋል። ሴናተሮች ህጉን ለማራዘም በሰጡት ድምፅ 51 ለ 49 ተቃውሞ ተመዝግባል። ይህ የተሰጠው ለዩክሬን የወደፊት ዕርዳታ ለመቀጠል እርግጠኛነት ላይ አጠራጣሪ አድርጎታል። የሕግ አውጭ አካላቱ ኮንግረሱ የክረምት ዕረፍት ከመውጣቱ ጥቂት ቀናት በፊት ጉዳዩን ወደ ድርድር ጠረጴዛው ይልካል ተብሎ ይጠበቃል።

እያንዳንዱ የሪፐብሊካን ሴናተር  ጨምሮ ከገለልተኛ ሴናተር በርኒ ሳንደርስ ጋር  በመሆን ርምጃውን ተቃውመዋል። ሕጉ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ወታደራዊ ዕርዳታ ለእስራኤል እንደሚጨምር የሚያደርግ በመሆኑ ያላቸውን ቅሬታ ገልፀዋል። የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በጋዛ ቀጠና እያካሄዱት ያለውን ዘመቻ በመጥቀስ፣ “ለቀኝ ጽንፈኛው ኔታንያሁ መንግሥት አሁን ያለውን ወታደራዊ አካሄድ ለመቀጠል ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ መመደብ አለብን ብዬ አላምንም” ብለዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎችን ገድሏል ሲሉ ሳንደርስ ተናግረዋል።

የኔታንያሁ የረዥም ጊዜ ተቺ የሆኑት ሳንደርስ አክለውም “የኔታንያሁ መንግስት እያደረገ ያለው ተግባር ኢ-ሞራላዊ ነው፣ አለም አቀፍ ህግን የጣሰ ነው፣ እናም አሜሪካ በድርጊቱ ተባባሪ መሆን የለባትም” ሲሉ አክለዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *