መደበኛ ያልሆነ

ዛሬ ታህሳስ 3፤2016 – እስራኤል በጋዛ በምትፈፅመው የቦምብ ጥቃት የተነሳ ዓለም አቀፍ ድጋፍ አጥታለች ሲሉ ባይደን ተናገሩ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እስራኤል በጋዛ ላይ እየፈፀመች ባለው አድሎአዊ የቦምብ ጥቃት ዓለም አቀፍ ድጋፍ ማጣት መጀመሯን ተናግረዋል። በትላንትናው እለት በተደረገ የገቢ ማሰባሰብያ ዝግጅት ላይ ለለጋሾች በሰጡት አስተያየት በእስራኤል አመራሮች ላይ ጠንካራ ትችትን ሰንዝረዋል። ሃማስ በጥቅምት 7 ጥቃቱን ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ባይደን ለእስራኤል የማይናወጥ ህዝባዊ ድጋፍ ሰጥተዋል።

እስራኤል በአሜሪካ ድጋፍ እንደምትተማመን ደጋግመው ባይደን ቢናገሩም ለእስራኤል መንግስት ግን ቀጥተኛ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። እ.ኤ.አ. በ 2024 እንደገና የመመረጥ ዘመቻውን ለጋሾች ሲናገሩ የእስራኤል ደህንነት በዩናይትድ ስቴትስ ላይ ብቻ የሚያተኩር አይደለም፣ በአውሮጳ ህብረት እና በአብዛኛው ዓለም በመሆኑ የቦምብ ጥቃተ ያንን ድጋፍ ማሳጣት ጀምሯል ብለዋል። ባይደን አክለውም ሀማስ ላይ ጥቃት መፈፀሟ ምንም ጥያቄ የለውም  እስራኤልም ይህንን ለማድረግ “ሙሉ መብት አላት” ብለዋል ።

የዩናይትድ ስቴትስ መሪ የእስራኤልን ወታደራዊ ዘመቻ እንዲቆጣጠሩ ከራሳቸው ዴሞክራቲክ ፓርቲ ጭምር ጫና ገጥሟቸዋል። ንግግራቸው በቅርቡ አስተዳደራቸው ከጀመረው ጦርነቱ ጋር የሚስማማ ሲሆን ባለሥልጣናቱ እስራኤል “ለሰው ልጅ ሕይወት ላይ ትልቅ ቦታ እንድትሰጥ” እና ግጭቱን እንድታስወግዱ የበለጠ ግልፅ መመሪያ እንድትሰጥ አሳስበዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ባለስልጣናት በእስራኤል ወታደራዊ ምላሽ ላይ ቅሬታቸውን እያሳዩ ይገኛሉ።

በጋዛ የሚገኘው በሃማስ የሚመራው የጤና ሚኒስቴር እንደገለጸው ከጥቅምት 7 ጀምሮ በእስራኤል በደረሰ የቦምብ ጥቃት ከ18,400 በላይ ሰዎች መገደላቸው ገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ማክሰኞ እለት በሰጡት መግለጫ እስራኤል ለምታካሂደው የምድር ጦርነት እንዲሁም ሃማስን ለማጥፋት እና ታጋቾችን ለማስመለስ ያላትን ዘመቻ ሙሉ ድጋፍ ከአሜሪካ አግኝታለች ብለዋል። አክለውም ዋሽንግተን ጦርነቱን ለማስቆም ዓለም አቀፍ ግፊትን እንዳስቆመች ገልፀዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *