መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 8፤2016 -ጣሊያን በጋዛ ቤተክርስትያን ላይ በደረሰው ጥቃት በእስራኤል ላይ ነቀፋ ሰነዘረች

የጣሊያን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ታጃኒ በእስራኤል ላይ በሰነዘሩት ያልተለመደ ትችት የእስራኤል ወታደሮች በጋዛ ቤተክርስትያን ውስጥ ሁለት ሴቶችን በጥይት ተኩሰው መተዋል ሲሉ ተናግረዋል። አንድ እስራኤላዊ ወታደር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የነበሩ ሁለት ሴቶች ላይ ተኩሷል።

ይህ ከሃማስ ጋር በሚደረገው ውጊያ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለውም ምክንያቱም አሸባሪዎቹ በእርግጠኝነት በአብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ተደብቀው ማለት አይቻልም ሲሉ ታጃኒ ገልፀዋል። በእየሩሳሌም የሚገኘው የላቲን ቤተ ክርስቲያን አንዲት ሴት እና ሴት ልጇ መገደላቸውን አስታውቋል። አክለውም ሰባት ሰዎች በጥቃቱ ቆስለዋል።

የእስራኤል የአየር ጥቃት 54 አካል ጉዳተኞች በተጠለሉበት ገዳም ላይ ጉዳት አድርሷል። ክስተቱ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ከባድ ትችት አስከትሏል። በሌላ በኩል በሰሜን ጋዛ ጃባሊያ እስራኤል በፈጸመችው የአየር ጥቃት ቢያንስ 110 ፍልስጤማውያን መሞታቸውን የሃማስ የጤና ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

በጥቃቱ ከእስራኤል የተሰጠ የተለየ አስተያየት የለም። እስራኤል የሃማስን መሠረተ ልማቶችን ኢላማ አድርጋለች። ጃባሊያ  ረዥም ዓመታት የስደተኞች ካምፕ ሲሆን በጋዛ ሰሜናዊ ክፍል ከጦርነቱ መጀመሪያ አንስቶ እስራኤል ሰዎች ለቀው እንዲወጡ ያስጠነቀቀችበት አካባቢ ነው ።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *