መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 10፤2016 –ማሌዥያ በጋዛ ወረራ ምክንያት የእስራኤልን መርከቦችን አገደች

???? እስራኤል በአንድ ቀን በፈፀመችው ጥቃት 100 የሚጠጉ ፍልስጥኤማውያን ተገደሉ

ማሌዥያ በጋዛ ወረራ ምክንያት የእስራኤል መርከቦች ወደ ባህር ክልሏእንዳይገቡ አግዳለች። የማሌዥያ የጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ጽህፈት ቤት በሰጠው ይፋዊ መግለጫ በዚም ማጓጓዣ ኩባንያ ላይ ፈጣን እገዳ የጣለው እስራኤል በጋዛ ፍልስጤማውያን ላይ ለወሰደችው እርምጃ ምላሽ ነው ብሏል። ፅህፈት ቤቱ ባወጣው መግለጫ እስራኤል በፍልስጤማውያን ላይ “እልቂት እና ጭካኔ” እየፈፀመች ነው ብሏል።

በተመሳሳይ ጊዜ ማሌዢያ የእስራኤል ባንዲራ የሰቀሉ መርከቦች ወደ ሀገሪቱ እንዳይገቡ ለማድረግ መወሰኗንም ተናግራለች። በተጨማሪም ማሌዢያ “ወደ እስራኤል የሚሄድ ማንኛውም መርከብ በማሌዢያ ወደቦች ላይ ጭነት እንዳይጭን እገዳ” ጥላለች። ሁለቱም ገደቦች ወዲያውኑ ወደ ተግባር እንደሚቀየሩ ተገልጿል።

እስራኤል በጋዛ በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ በፈፀመችው ጥቃት ወደ 100 የሚጠጉ ፍልስጤማውያንን ሲገደሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ቆስለዋል ሲል የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በሌላ በኩል የእስራኤሉ ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ ከጋዛ ተጨማሪ ምርኮኞችን ለማስፈታት ሀገራቸው ለሁለተኛ ጊዜ ሰብአዊ እረፍት ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል ። የሐማስ ከፍተኛ መሪ እስማኤል ሃኒዬህ የተኩስ አቁም እና የእስረኞች ልውውጥ ለማድረግ በዛሬው እለት ግብፅን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *