መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 10፤2016 –በያቤሎ ከተማ አንዲት እናት አራት ልጆችን በሰላም መገላገሏ ተሰማ

በያቤሎ አጠቃላይ ሪፈራል ሆስፒታል  አንዲት  እናት በአንድ ጊዜ አራት ህጻናት በሰላም መገላገሏን የያቤሎ አጠቃላይ ሪፈራል ሆስፒታል መግለጹን ብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ሰምቷል።

ታህሳስ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ረፋድ ላይ የ39 ዓመት እድሜ ያላት እናት የሆነች ግለሰብ  በቦረና ዞን አሌዋዮ ከተባለ ስፍራ  ያቤሎ አጠቃላይ ሆስፒታል  ለወሊድ በገባችበት አራት ልጆች በሰላም መገላገሏም ተገልጿል።

በተጨማሪም  ሶስቱን ልጆች በምጥ ስትወልድ አንዱን ደግሞ በቀዶ ህክምና ተገላግላለች። ህጻናቱ  2.2 እና 2.4 ኪሎ የሚመዝኑ መሆኑን  እንዲሁም  ሶስት ወንድ እና አንድ ሴት መሆናቸው ተመላክቷል። እናቲቱ እና ህፃናቱ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙም ተነግሯል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *