መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 11፤2016 –ቼክ ሪፐብሊክ የነገው እለት ብሄራዊ ሀዘን ነው ስትል አወጀች

ቼክ ሪፐብሊክ በፕራግ በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አንድ ታጣቂ 14 ሰዎችን ከገደለ እና 25 ሰዎችን ካቆሰለ በኋላ ነገ ቅዳሜ ብሔራዊ የሀዘን ቀን ነው ስትል አውጇለች። ፕሬዘደንት ፔትር ፓቬል በደረሰው የህይወት መጥፋት “ታላቅ ሀዘን” እና “በፍፁም አላስፈላጊ በሆነው” የህይወት መጥፋት ንዴታቸውን ገልጸዋል። ፖሊስ “ተወግዷል” ያለው ታጣቂው አባቱን እንደገደለ እና ምናልባትም ባለፈው ሳምንት ከሁለት ሰዎች ሞት ጋር የተያያዘ ወንጀለኛ ሊሆን ይችላል ብሏል።

በቅርብ ዓመታት የአውሮጳ ታሪክ ውስጥ ከታዩት የጅምላ ጥቃቶች አንዱ ነው። በቼክ ዋና ከተማ መሀል በሚገኘው የቻርለስ ዩኒቨርሲቲ የስነ ጥበባት ፋኩልቲ ህንፃ ላይ ሐሙስ እለት ጥቃቱ ተከፍቷል። ታጣቂው በህንፃው ኮሪደሮች እና የመማሪያ ክፍሎች ውስጥ ተኩስ የከፈተ ሲሆን በዘፈቀደ በመተኮስ በርካቶችን ለሞት እና ለጉዳት ዳርጓ።ሰራተኞቹ እና ተማሪዎች የመማሪያ ክፍል እና የቢሮ እቃዎችን በመሸፈን ራሳቸውን ሲከላከሉ ታይተዋል። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተጋሩ ቪዲዮዎች እንዳሳዩት ሰዎች ራሳቸውን ለማስጣል ከከፍታ ላይ ሲዘሉ ላይ ያሳያል። የተኩስ ድምጽም ይሰማል።

ፖሊስ ታጣቂው የ24 ዓመቱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረ እና ከዚህ ቀደም ምንም አይነት የወንጀል ሪከርድ ያልነበረው ቢሆንም፣ “ትልቅ የጦር መሳሪያ እና ጥይቶች” ማገኘቱን ገልጿል።

ከመተኮሱ በፊት ፖሊስ ተጠርጣሪው ራሱን ለመግደል በማሰብ በአቅራቢያው ካለ ከተማ ወደ ፕራግ ማምራቱን ሪፖርት ደርሶታል። ከጥቂት ጊዜ በኋላ የሰውየው አባት ሞቶ ተገኝቷል። በተኩሱ ከቆሰሉት 25 ሰዎች መካከል 10 ያህሉ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተነግሯል። የቼክ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔትር ፊያላ በሰጡት መግለጫ ይህ አሰቃቂ ድርጊት ሁላችንም አስደንግጠናል ብለዋል።

በአንድ በኩል ድርጊቱን ለማውገዝ ቃላትን ለማግኘት አስቸጋሪ ነው፤  በሌላ በኩል ደግሞ መላው ህዝባች። ከገና ከፊት ባሉት ቀናት ውስጥ የሚሰማውን ህመም እና ሀዘን ከባድ ነው ለዚህም ቅዳሜ የሐዘን ቀን እንደሚሆን ገልፀዋል። በሁሉም የሕዝብ ሕንፃዎች ላይ ባንዲራ ዝቅ ብሎ እንደሚውለበለብና እኩለ ቀን ላይ የአንድ ደቂቃ ጸጥታ እንደሚከበርም ተናግረዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *