መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 15፤2016 – አይቴል ሞባይል አርቲስት ኑሃሚን መሰረትን ብራንድ አምባሳደረ አድርጎ ሾመ

አይቴል ኢትዮጽያ ሞባይል  ከ16 ከዓመታት በላይ ሲሰራ የቆየ እና አዳዲስ ምርቶችን ለገበያ ሲያቀርብ  የነበረ መሆኑ የአይቴል ብራንድ አምባሳደር የሆኑት ኢሞን  ጂያ  ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

በመሆኑም በዛሬው ዕለት  አዳዲስ የሚያመርታቸውን ምርቶች  ለማስተዋወቅ በብራንድ አምባሳደር አድርጎ አርቲስት ኑሃሚን መሰረትን ሾሟል።

ከ10 በላይ የተለያዩ ሞዴሎች ያሉት ሲሆን  አሁንም በአዲስ መልክ አዳዲስ ምርቶችን ለገበያ ለማቅረብ ማቀዱን  ተገልጿል ። በቅርቡ ይፋ ያደረገው የመለያ ምልክት ለውጥ እና የአስተዳደር ለውጥ አስመልክቶ በምርቱ ላይ ትልቅ የሆነ ለውጥ እንደሚያመጣ ተጠቁሟል።

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ከሆኑት የስማርት ሞባይል ስልኮች መካከል የሚጠቀስ መሆኑ በራሱ ትልቅ ሃላፊነት የሚጥል እንደሆነ የአይቴል ብራንድ አምባሳደር የሆኑት  ኢሞን  ጂያ ጨምረውም ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል  ።

በኤደን ሽመልስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *