መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 15፤2016 -ጄኔራል ቡርሃን የዋድ ማዳኒ ከተማን የአርኤስኤፍ ኃይሎች የያዙት በጦሩ ቸልተኝነት ነው ሲሉ ተናገሩ

የሱዳን ጦር አዛዥ  አብዱልፈታህ አል ቡርሃን የዋድ ማዳኒ ከተማ በአርኤስኤፍ ኃይሎች ስር የወደቀችው በሱዳን ጦር ቸልተኝነት በማለት የጦር አዛዦችን ወቀሱ።

ሰራዊቱ የገዚራ ግዛት ዋና ከተማን ለቆ ሲወጣ ተከትሎ አይነት ውጊያ ሳያደርግ ቀርቷል በሚል ተወቅሷል። ከ300,000 በላይ ሰዎች ከገዚራ ከተማ ለቀው ተሰደዋል። የዋድ ማዳኒ ከተማ በአርኤስኤፍ ወይም በሱዳን የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች እጅ ስር ከወደቀች ከአራት ቀናት በኋላ ጄኔራል አብዱልፈታህ አል-ቡርሃን ጉዳዩን በይፋ ተናግረዋል።

ቸልተኛ የጦር አዛዦችን ሁሉ ተጠያቂ እናደርጋለን። ያለ ርህራሄ ተጠያቂ ይሆናሉ ሲሉም አክለዋል የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሃይሎች ዋድ ማዳኒን ከተማ እንዲቆጣጠር ያስቻለውን አስገራሚውን ማፈግፈግ እንደሚመረምር የሱዳን ጦር ተናግሯል። አርኤስኤፍ የጌዚራ ግዛት ሙሉ በሙሉ መያዙን ይገልጻለ። ሆኖም ግጭቱ መስፋፋቱ በመቀጠሉ የእርዳታ ሰራተኞች ከአጎራባች አካባቢዎች እየሸሹ ይገኛል።

ካለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር ጀምሮ ከሰራዊቱ ጋር እየተዋጋ ያለው አርኤስኤፍ 70 በመቶ የሚጠጋውን የሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም እና አብዛኛውን የምዕራብ ዳርፉር ክልል እንደተቆጣጠር ይታመናል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደ ካርቱም ካሉ አደገኛ አካባቢዎች ወደ ገዚራ እና ዋድ ማዳኒ ተሰደው ነበር።

በሌላ በኩል የሱዳን ጦር እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ውዝግብ ውስጥ መግባታቸው ተሰምቷል። በጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሀን የሚመራው ጦር በጦርነቱ ተቀናቃኛቸው ለሆኑይ ጄኔራል መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎንን የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ትደግፋለች በሚል ከሰዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *