መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 17፤2016 – በአሶሳ ዞን የፍቅር ጥያቄን ለመቀበል ፍቃደኛ አይደለችም በማለት የግድያ ወንጀል የፈፀመዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በአሶሳ ዞን በባምባሲ  ወረዳ  የ03 ቀበሌ  ነዋሪ የሆነውን ብርሃኑ ሞላ ፀጋየ የተባለ ግለሰብ  የወንጀል ድርጊቱን የፈጸመዉ በእለተ እሁድ የካቲት  19 ቀን 2015 ዓ/ም በግምት ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ላይ ነበር፡፡

የግል ተበዳይ ሟች  ትዕግስት ተሰማ   የተባለቹን ግለሰብ ግድያ መፈፀሙን የአሶሳ ዞን ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ኢንስፔክተር  መንገሻ አበበ ለብስራት ቴሌቪዥንና ራዲዮ ገልፀዋል።አብረዉ ሰርግ ቦታ ሲጫወት ውለዉ  አብረው ካመሹ በኃላ ብዙ ገንዘቤን አዉጥቼ ባዝናናትም አብራኝ ልትሆን ፍቃደኛ አልሆነችም ብሏል፡፡

ቂም በመያዝ አመቺ ጊዜ ጠብቆ ጨለማን ተገን በማድረግ በምሽት ማንም ሰዉ የለሌበት ቦታ በመዉሰድ በአሰቃቂ ሁኔታ ደብድቦ   በተለያየ የሰዉነት ክፍሏ ላይ ጉዳት በማድረስ   በባምባሲ ከተማ 01 ቀበሌ ዉስጥ ባምባሲ ስደተኞች ካምፕ አካባቢ ድርጊቱን  እንደፈፀመዉ ተረጋግጧል፡፡ግለሰብ በፈፀመው  ጭካኔ የተሞላበት ፣ ነዉረኛና አደገኝነት በሚገልፅ ሁኔታ ከባድ የሰው ግድያ  ወንጀል ተከሷል። 

ዐቃቤ ህግና መርማሪ ፖሊስ በጋራ በመሆን በተጠርጣሪው ላይ ምርመራ  በማጣራት የወንጀል ድርጊቱን በሚያስረዱ የሰው፣ የሰነድና የህክምና ማስረጃ በማስደገፍ  ተጠርጣሪው ላይ ክስ መስርተዋል ።

የክስ መዝገቡ የደረሰው የአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም  መዝገቡን ሲመርምር ከቆየ በኃላ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ .ዲ.ሪ የወንጀል ህግ /አንቀጽ /539 (1/ሀ) የተመለከተውን በመተላለፉ በፈፀመዉ ድርጊት ከእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እስከ  ሞት ቅጣት እንደሚያስቀጣ  ተናግረዋል።

ነገር ግን ፍቤቱ የቅጣት ማካበጃና ማቀለያ ግምት ውስጥ በማስገባት ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት በ 13 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ማሳለፉን ኢንስፔክተር መንገሻ አበበ ለብስራት ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ጨምረዉ ተናግረዋል።

በበቀለ ጌታሁን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *