መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 22፤2016-በተሳሳተ የስልክ ጥሪ ትዳር ከመስርተ በኋላ ከባለቤቱ በመለያየቱ ራሱን ያጠፋው ግለሰብ ድርጊት የፍቼ ከተማ ነዋሪዎችን አስደነገጠ

ማንደፍሮ እንዳለ የተባለ ግለሰብ በደብረማርቆስ ከተማ የተለያዩ የቦንዳ አልባሳትን በማዞር የሚተዳደር ግለሰብ ነበር።

ከስምንት አመት በፊት በተሳሳተ የስልክ ጥሪ ከዛሬ ባለቤቱ ጋር ትውውቅ ይፈጥራሉ።ባለቤቱ ብቻ በቅቱ በፍቼ ከተማ አዲስ ሰፈር ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ሽንኩርት ፣ድንችና አትክልቶችን በመሸጥ ትኖር ነበር።ይህችው ወጣት አትክልት ለሚያስመጣላት ልጅ ደወልኩ በማለት በስህተት ከወቅቱ ባለቤቷ ጋር መተዋወቀቸውን የፍቼ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ወንጀል ምርመራ ክፍል ሃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ፈቃዱ ንጉሴ ለብስራት ቲቪና ራዲዮ ተናግረዋል።

በስህተት ከደወለች ቀን አንስቶ ከልጁ ጋር በመተዋወቅ በቀን እስከ 2 ጊዜ መደዋወል ይጀምራሉ።ማንደፍሮ የተባለው ግለሰብም ለምን ደብረማርቆስ አትመጭም ሲላት እሷም በሃሳቡ በመስማማት ደብረማርቆስ ትሄድና አብረዉ መኖር ይጀምራሉ። የባልትና ንግድ ስትጀምር እሱ ደግሞ የተለያዩ የቦንዳ አልባሳትን እየተዘዋወረ በመሸጥ አንዲት ሴት ልጅ ይወልዳሉ።

በደብረማርቆስ ከተማ ስራ እየሰሩ እያለ ስራው ሲቀዛቀዝ ተያይዘዉ ወደ ፍቼ ከተማ ያመራሉ።በፍቼ ከተማ ባመሩበት የማንደፍሮ አጎቱ በቢራ ፋብሪካ አከፋፋይ ውስጥ ይሰራ ስለነበር በድራፍት ማሽን ማጠብ ሰራ ያስቀጥረዋል።ባለቤቱ የተለመደዉን ስራዋን እየሰራች እያለ ከሌላ የወለደችው ልጅ እንዳላት ሲያዉቅ አለመግባባት ይፈጠራል።

ግጭቱ የተፈጠረበት ምክንያት ሚስቱ ከሌላ ለወለድሽው ልጇ  ለምን ስልክ ትገዣለሽ  በሚል ወደ ክስ ያመራሉ።የፍቼ ከተማ ፖሊስ በሽምግልና እንዲፈታ ቢሞክርም ባለማሳካቱ ወደ ፍርድ ቤት ይልካቸዋል።ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን ካየ በኋላ እንደገና በሽምግልና እንዲፈታ ያዛል።

ሽማግሌዎችም ለማስታረቅ ቀን ቀጥረዉ እያለ በአጋጣሚ ከሽማግሌዎች አንዱ ሀዘን ይገጥመዉና ለሌላ ቀን ይቀጠራል ።በዚህ ጊዜ 5 ገፅ ደብዳቤ በመፃፍ  በብስጭት ከባለቤቱ ጋር በስልክ ካወራ በኋላ በጓደኛው ቤት ውስጥ ራሱን ያጠፋል።ጓደኛዉ ወደ ቤቱ ሲመለስ ራሱን አጥፍቶ ያገኘዋል።ልጁም ለፍቼ ከተማ ፖሊስ ወዲያውኑ ያመለክታል።

የፍቼ ከተማ ፖሊስም ከአስከሬኑ ጋር 5 ገፅ ደብዳቤ ያገኛል ።በደብዳቤዉ ላይ ራሱን እንዳጠፋና ሚስቱን ለማጥፋት እንዳሰበ  ነገር ግን ለልጁ ሲል እንደተዋት የፍቼ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ወንጀል ምርመራ ክፍል ሃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ፈቃዱ ንጉሴ ለብስራት ቲቪና ራዲዮ ተናግረዋል።

በበቀለ ጌታሁን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *