ጦማር/ዜና

ሚያዝያ 15፣ 2012-ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ከእስር ተለቀቀ

ሐሰተኛ መረጃን በማሰራጨት በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት እና ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ የቆየው ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ዛሬ ሚያዚያ 15/2012 ከዕስር መለቀቃቸውን የጋዜጠኛው ጠበቃ ታደለ ገብረመድሕን ለአዲስ ማለዳ አስታወቁ።

ጋዜጠኛው በ15 ሽሕ ብር ዋስ ከእስር ወጥተው ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ፍርድ ቤቱ ወስኗል። ጋዜጠኛው ከዚህ ቀደም ኹለት ጊዜያት የዋስትና መብታቸው በፍርድ ቤት ተከብሮላቸው እንዲወጡ ተወስኖ እንደነበር የሚታወስ ነው።

ጦማር/ዜና

ሚያዝያ 15፣ 2012-በታይላንድ የአንድ ወር እድሜ ያለዉ ጨቅላ ህጻን ከኮሮና ቫይረስ ማገገሙ ተሰማ

የህክምና ባለሙያዎች ህጻኑ ከቫይረሱ እንዲያገግም አራት የፀረ-ቫይረስ መድሃኒቶችን መጠቀማቸዉን አስታዉቀዋል፡፡ይህንን ህክምና ባለሙያዎቹ ለ10 ቀናት ለህጻኑ ሰጥተዋል፡፡

በኤክስ ሬይ በተደረገለት ምርመራ ከቫይረሱ ሙሉ ለሙሉ ማገገሙ ተረጋግጧል፡፡በታይላንድ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ የ50 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

ጦማር/ዜና

ሚያዝያ 15፣ 2012-የተባበሩት ድርጅት የህጻናት መርጃ ድርጅት(UNICEF) በኢትዮጵያ ለኮሮናቫይረስ መከላከያ የሚውል 1.5 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቀሰ ድጋፍ አደረገ

ድጋፍ የተደረገው የህክምና ቁሳቀስ ሙሉ በሙሉ ለጤና ባለሙያዎች የሚሰጥ ሲሆን ፤
የፊት መሸፈኛ ጭንብል ፣ የሙቀት መለኪያ መሣሪያና የህክምና አልባሳትን የሚያካትት
ነው።

የኢትዮጵያ የመድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የህክምና ቁሳቁሶቹን ለየክልሎች የሚያከፋፍል መሆኑም ተገልጿል።

ድርጅቱ ድጋፉን ያደረገው በራሱና በእንግሊዝ መንግሥት እርዳታ መሆኑ ተጠቁሟል።

በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ተወካይ አዴል ኮድር ድጋፉን ለጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ
ማስረከባቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

ጦማር/ዜና

ሚያዝያ 15፣ 2012-የፊላንድ ጠቅላይ ሚንስትር ሳና ማሪን ራሷን ማግለሏ ተሰማ

በጠቅላይ ሚንስትሯ የመኖሪያ ስፍራ በኮሮና ቫይረስ መያዙ የተረጋገጠ ሰዉ ጋር ሳና ማሪን የቅርብ ንኪኪ እንደነበራት ተነግሯል፡፡ለጠቅላይ ሚንስትሯ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ምልክት እንዳልታየባት የፊላንድ ጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ይፋ አድርጓል፡፡

ሳና ማሪን የአለማችን ወጣቷ ጠቅላይ ሚንስትር በመባል በመላዉ ዓለም እዉቅናን ማግኘት የቻለች ሲሆን በ34 ዓመቷ በታህሳስ ወር የፊላንድ ጠቅላይ ሚንስትር መባሏ ይታወሳል፡፡በፊላንድ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ የ149 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

ጦማር/ዜና

ሚያዝያ 15፣ 2012-ኮሮና ቫይረስ ያስተዋወቃቸዉ ፍቅረኛሞች ጋብቻቸዉን ፈጸሙ

ከአንድ ወር በፊት የ39 ዓመቷ ኦሶሪዮ የግዳጅ ለይቶ ማቆያ በኮሎምቢያ ሲተገበር በቂ የሚባል ገንዘብ ስላልነበራት ራሷን እንድታቆይ የተገደደችዉ መንግስት ባዘጋጀዉ መጠለያ ዉስጥ ነበር፡፡

መጠለያዉ የቡና እርሻ ባለበት የኮሎምቢያ ግዛት ዉስጥ ነዉ፡፡የ72 ዓመቱ አርዲላ የግንባታ ባለሙያ ሲሆን በኮሮና ምክንያት ስራ ቀዝቅዟል፤ከዚህም በተጨማሪ የጭንቀላት ጉዳት አጋጥሞት የቤት ኪራይ መክፈል ባለመቻሉ ወደ መጠለያ ለመግባት ይገደዳል፡፡

በዚህ ስፍራ ሳለ ታዲያ ስለ እርሱ ማንም ግድ እንደማይሰጠዉ ይናገራል፡፡ሆኖም ግን ይህቺ ሴት ስለ እርሱ መጨነቋ ይበልጥ ትኩረቱ ይስበዋል፡፡ይህ መተሳሰብ እና መቀራረብ ወደ ፍቅር አድጎ በቀናት ልዩነት በጋብቻ ተጣምረዋል፡፡

በዚሁ የመጠለያ ስፍራ ጋብቻቸዉን የፈፀሙ ሲሆን በመጠለያዉ የተለየ ስፍራ ለጥንዶቹ መሰጠቱ ተሰምቷል፡፡

ጦማር/ዜና

ሚያዝያ 15፣ 2012 -በፍሎሪዳ የሚገኙ ፖሊሶች ለህክምና ባለሙያዎች ክብር ሲሉ በመኪናቸዉ ልብ ቅርጽ በመስራት ምስጋናቸዉን ገልጸዋል

በፍሎሪዳ የሚገኙ ፖሊሶች ለህክምና ባለሙያዎች ክብር ሲሉ በመኪናቸዉ ልብ ቅርጽ በመስራት ምስጋናቸዉን ገልጸዋል፡፡

በፍሎሪዳ የሚገኙት የፖሊስ አባላት በከተማዋ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ጥረት እያደረጉ የሚገኙ የህክምና ባለሙያዎችን ለማመስገን በሆስፒታሉ የመኪና ማቆሚያ ስፍራ የልብ ቅርጽን በመኪናቸዉ በመስራት ምስጋናቸዉን ገልጸዋል፡፡

ጦማር/ዜና

ሚያዝያ 15፣ 2012 -የአለም የጤና ድርጅት ቢጫ ወባ በኢትዮጵያ ሊስፋፋ እንደሚችል አስጠነቀቀ

የአለም የጤና ድርጅት ቢጫ ወባ በኢትዮጵያ ሊስፋፋ እንደሚችል አስጠነቀቀ

ከመጋቢት መጀመሪያ አንስቶ በኢትዮጲያ በቢጫ ወባ መያዛቸዉ የተለዩ ሰዎች ቁጥር ከሶስት ወደ 86 በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ከፍ ብሏል፡፡
ከተለዩት ሰዎች መካከል ስምንቱ ቢጫ ወባ የተገኘባቸዉ ሲሆን በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ክልል በጉራጌ ዞን ገጠራማ ስፍራዎች ዉስጥ ስለመሆኑ የአለም የጤና ድርጅት ይፋ አድጓል፡፡

ጦማር/ዜና

ሚያዝያ 15፣ 2012 -የሴራሊዮን ፕሬዚዳንት የግል ጠባቂ በኮሮና ቫይረስ መያዙን ተከትሎ ፤ ፕሬዚደንቱ ራሳቸውን እንዲያገሉ ሆኗል

የሴራሊዮን ፕሬዚዳንት የግል ጠባቂ በኮሮና ቫይረስ መያዙን ተከትሎ ፤ ፕሬዚደንቱ ራሳቸውን እንዲያገሉ ሆኗል።

ፕሬዚዳንት ጁሊየስ ማዳ_ባዮ የግል ጠባቂያቸው በቫይረሱ መጠቃቱን ተከትሎ ለአስራ አራት ቀናት የሚደረግላቸው ክትትል ካሳለፍነዉ ሰኞ ጀምረዋል።

እርሳቸው ለይቶ ማቆያ ላይ ቢሆኑም እንኳ የሚደረጉ የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች እንደማይቋረጥ ፤ ሃሳብ አይግባችሁ ሲሉ ለሴራሊዮናውያን በአይሀራሪ የዜና ወኪል በኩል አስታውቀዋል።

በእርሳቸውና ቤተሰባቸው ላይ እስካሁን ምንም አይነት ምልክት አለመታየቱንና ፤ በፍፁም ጤና ላይ እንደሚገኙም ገልፀዋል።

ጦማር/ዜና

ሚያዝያ 14፣ 2012-አንድ የቻይና ባለስልጣን የአዉስትራሊያን የሀገር ዉስጥ ጉዳይ ሚንስትርን የአሜሪካ አሻንጉሊት ማለታቸዉ ተሰማ

የአዉስትራሊያ የሀገር ዉስጥ ጉዳይ ሚንስትር ፒተር ዶቶን ቻይና በኮሮና ቫይረስ መዛመት ዙሪያ ግልጽነት ይጎድላታል ስለዚህ ግልጽ ትሁን ሲል ጥሪ ያቀርባል፡፡

በአዉስትራሊያ የሚገኘዉ የቻይና ኤምባሲ ከፍተኛ የስራ ሀላፊ ከአሜሪካ የተቀበለዉን መመሪያ አቅርቧል፤የአሜሪካ አሻንጉሊት ሲሉ መጥራታቸዉ ተሰምቷል፡፡

ጦማር/ዜና

ሚያዝያ 14፣ 2012-በቋራ ወረዳ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪ ተያዘ

በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውር የተገኘ አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ገለፀ ፡፡

የቋራ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ተወካይ ኃላፊ ዋና ሳጅን ዳምጠው ሞላ ለኢዜአ እንደተናገሩት ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር የዋለው ሚያዚያ 12 ቀን 2012 ዓም ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ በወረዳው ነብስ ገበያ ቁጥር አንድ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተለያዩ ጥይቶችን ይዞ ሲንቀሳቀስ በመገኘቱ ነው ።

ግለሰቡ የሰሌዳ ቁጥር በሌለው ሞተር ሳይክል ሲንቀሳቀስ 1 ሺህ 142 የክላሽኮቭና 500 የብሬን ጥይቶች እንዲሁም 38 የክላሽን ካዝናዎች ይዞ መገኘቱን ገልፀዋል።

ወረዳው ከሱዳን ጋር የሚዋሰን በመሆኑ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል በወጣው አዋጅ መሰረት የፀጥታ አካላት ቁጥጥር በሚያደርጉበት ወቅት ግለሰቡ እንደተያዘም ዋና ሳጅኑ ተናግረዋል ።