ጦማር/ዜና

ሚያዝያ 14፣ 2012-በድሬዳዋ አስተዳደር የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በገንዘብና በዓይነት 17 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ድጋፍ መሰብሰቡን በአስተዳደሩ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታወቀ

በድሬዳዋ አስተዳደር የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በገንዘብና በዓይነት 17 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ድጋፍ መሰብሰቡን በአስተዳደሩ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

ከዚህ ውስጥ 8 ሚሊዮን ብር በጥሬ ገንዘብ ቀሪው ደግሞ በዓይነት ተሰብስቧል፤ የተሰበሰበው ገቢም ወደ ድሬዳዋ ስጋት አመራርና አደጋ መከላከል ጽ/ቤት እንዲገባ መደረጉንም ተሰምቷል፡፡

ጦማር/ዜና

ሚያዝያ 14፣ 2012-በግብጽ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ፍትህ ለታራሚዎች ሲል ድምጹን ያሰማዉ የህክምና ተማሪ በእስር ላይ ይገኛል

የህክምና ተማሪ የሆነዉ ሞሃመድ አሜሻ በካይሮ በሚገኘዉ ታህሪሪ አደባባይ ፍትህ ለታራሚዎች የሚል የተቃዉሞ ድምጽ ያሰማል፡፡የግብጽ መንግስት እርሱን ከማሰር ሳይቆጠብ በቁጥጥር ስር አዉሎት ይገኛል፡፡

ቤተሰቦቹ እንዳስታወቁት አሜሻ የረሃብ አድማ ማድረጉን እና በአስም እየተሰቃየ መሆኑን ተናግረዋል፡፡የግብጽ መንግስት አሜሽን ጨምሮ 114,000 ታራሚዎችን በቁጥጥር ስር አዉሎ ይገኛል፡፡

3‚490 ሰዎች በቫይረሱ በተያዙባት ግብጽ የ264 ሰዎች ህልፈት ሪፖርት የተደረገ ሲሆን የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በሀሰት የተወነጀሉ ዜጎችን እንዲለቅ የካይሮ መንግስት ጫና እየተደረገበት ይገኛል፡፡

ጦማር/ዜና

ሚያዝያ 14፣ 2012-በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ

በኢትዮጵያ ባለፋት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 1073 የላብራቶሪ ምርመራ ሁለት (2) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋግጧል። በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 116 ደርሷል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 – የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊ የመኖሪያ ቦታው በአፋል ክልል ገዋኔ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ግንኙነት በመጣራት ላይ ነው።

ታማሚ 2 – የ54 ዓመት አሜሪካዊ (በትውልድ ኢትዮጵያዊ) ከአሜሪካ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ጦማር/ዜና

ሚያዝያ 14፣ 2012-አጫጭር መረጃዎች

~ በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ እንቅስቃሴን የሚከለክለዉን ህግ የተቃወሙ ወጣቶች ከፖሊስ ጋር መጋጨታቸዉ ተሰማ፡፡በከተማዋ ሁለት አካባቢዎች ግጭት የነበረ ሲሆን ተሸከርካሪዎች በእሳት እንዲጋዩ ተደርጓል፡፡

~ የኮሮና ቫይረስ እንዴት ሊቀሰቀስ እንደቻለና ስርጭቱን በተመለከተ የአለም የጤና ድርጅትን ምላሽ በተመለከተ አዉስትራሊያና አሜሪካ በምርመራዉ ዙሪያ ዉይይት አደረጉ፡፡የአዉስትራሊያ ጠ/ሚ ሞሪሰን ከትራምፕ ጋር የስልክ ዉይይት አድርገዋል፡፡

~ ሰሜን አዉሮጳዊቷ ሀገር ኒዉዝላንድ ዜጎቿን ለመደገፍ የሚያስችል አዲስ የእርዳታ ጥቅላ ማዘጋጀቷ ተሰማ፡፡42 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ሲበጀት ለአነስተኛ የንግድ ስራዎችና ለስራ አጦች የሚዉል ነው፡፡

~ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ በሩዋንዳ ኪጋሊ ሊካሄድ የነበረዉ የኮመንዌልዝ ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ እንዲተላለፍ ተደረገ፡፡በ26ኛ የመሪዎች ጉባኤ የእንግሊዝ ጠ/ሚ እና በዌልስ ልዑሉን ጨምሮ ከ10ሺ በላይ ልዑካን ይታደማሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡የኮመንዌልዝ ሀገራት የሚባሉት በእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ ስር የነበሩ ናቸዉ፡፡

~ ዶናልድ ትራምፕ ለኑሮ ወደ አሜሪካ የሚደረግ ጉዞን ለ60 ቀናት የሚከለክለዉን መመሪያ ከሰዓታት በኃላ ይፈርማሉ፡፡ህጉ በጊዜአዊነት ወደ አሜሪካ የሚያቀኑትን አይመለከትም፡፡ትራምፕ ለኮሮና ተገቢዉን ምላሽ አለመስጠታቸዉን ተከትሎ በዚህ ለማካካስ ጥረት እያደረጉ ይገኛል የሚል ትችት ቀርቦባቸዋል፡፡

~ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ባንኮች፣የምግብና የንግድ ተቋማት በኪንሻሳ ከዛሬ ጀምሮ እንደሚከፈቱ አስታወቀች፡፡የ25 ሰዎች ህልፈት ሪፖርት ሲደረግ 350 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

~ የስፔን ጠቅላይ ሚንስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ከወርሃ ግንቦት በኃላ እንቅስቃሴን የሚከለክለዉ ህግ ቀስ በቀስ እንደሚነሳ አስታወቁ፡፡

ጦማር/ዜና

ሚያዝያ 14፣ 2012-የስቴፈን ሀውኪንግ ነበረ የተባለዉ የመተንፈሻ እገዛ መሳሪያ ለእንግሊዝ ብሄራዊ የጤና አገልግሎት ተለገሰ

በፊዚክስ እና በህዋ ሳይንስ በርካታ ስራዎችን ለአለም ያበረከተዉ ስቴፈን ሀውኪንግ በ2018 በነርቭ በሽታ ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል፡፡የስቴፈን ሀውኪንግ የመተንፈሻ እገዛ መሳሪያ ለኮሮና ህሙማን ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል ተብሏል፡፡

ዩናይትድ ኪንግደም 10,000 የሚጠጉ የመተንፈሻ እገዛ መሳሪያ ያላት ሲሆን የጤና ዋና ፀሀፊዉ ማት ሀንኩክ 18ሺ የመተንፈሻ እገዛ መሳሪያ እንደሚያስፈልግ መናገራቸዉ ይታወሳል፡፡

ጦማር/ዜና

ሚያዝያ 14፣ 2012-በህንድ የሚገኘዉ ግዙፉ የአትክልትና ፍራፍሬ ገበያ ሊዘጋ መሆኑ ተሰማ

በህንድ የሚገኘዉ ግዙፉ የአትክልትና ፍራፍሬ ገበያ ሊዘጋ መሆኑ ተሰማ

አዝዛርፉል ማንዲ በተባለዉ የገበያ ስፍራ አንድ ነጋዴ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ ህይወቱ ማለፉን ተከትሎ ሸማቾች የገበያ ስፍራዊ እንዲዘጋ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛል፡፡አንዳንድ ነጋዴዎች በቫይረሱ የመዛመት ፍራቻ የተነሳ ሱቃቸዉን ዘግተዋል፡፡

አዝዛርፉል ማንዲ የተሰኘዉ የገበያ ስፍራ በቀን ከ200ሺ በላይ ሰዎች የሚጎበኙት ሲሆን በ31 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ነዉ፡፡

ጦማር/ዜና

ሚያዝያ 14፣ 2012 -አይኤስ(ዳኢሽን) ተቀላቅሎ የነበረዉ ራፐር በስፔን በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰማ

አይኤስ(ዳኢሽን) ተቀላቅሎ የነበረዉ ራፐር በስፔን በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰማ

ነዋሪነቱ በለንደን የነበረዉ የ28 ዓመቱ አብደል ማጂድ አብድለ ባሪ በ2013 በአይኤስ ፕሮፖጋንዳ ተማርኮ ለንደንን ጥሎ ወደ ሶርያ በማቅናት ቡድኑን ይቀላቀላል፡፡

አይኤስ(ዳኢሽ) የተለያዩ ምስሎችን በማህበራዊ ገጽ ሲለቅም ይህዉ ሰዉ በብዛት ይታይ ነበር፡፡የቡድኑን መዳከም ተከትሎ ዳግም በህገወጥ መልኩ ከሶርያ ስፔን ይገባል፡፡በስፔን አልሜሪያ ከጓደኞቹ ጋር በድብቅ ተከራይቶ ከሚኖርበት አፓርታማ በፖሊስ በቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡

የአደል ባሪ ወላጅ አባት እ.ኤ.አ በ1998 በኬንያና ታንዛኒያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲዎች በአል ቃይዳ በደረሱ ጥቃቶች ጥፋተኛ መባላቸዉ ይታወሳል፡፡

ጦማር/ዜና

ሚያዝያ 14፣ 2012 -የሞዛምቢክ መንግስት ከፖላንድ ዶሮ እንዳይገባ እገዳ ማድረጉን አስታወቀ

የሞዛምቢክ መንግስት ከፖላንድ ዶሮ እንዳይገባ እገዳ ማድረጉን አስታወቀ

የአዉሮጳ የምግብ ደህንነት ባለስልጣን ለጤና ጎጂ የሆነ ሳልሞኔላ ቀዝቅዞ እና በተከማቸ ዶሮ ዉስጥ ይገኛል ማለቱን ተከትሎ እርምጃዉ ተግባራዊ ሆኗል፡፡

እነዚህ ዶሮዎች የተመገቡ ሰዎች ከ16 እስከ 32 ሰዓታት ዉስጥ ለተቅማጥ፣ለሆድ ህመምና ትኩሳት የሚጋለጡ ሲሆን ያለ ህክምና እንደሚያገግሙ ተነግሯል፡፡ይህንን ተከትሎ የፖላንድ የዶሮ አቅራቢዉ ሱፐርድሮብን የሞዛምቢክ መንግስት አግዷል፡፡

ጦማር/ዜና

ሚያዝያ 14፣ 2012-በጡት ማስያዣዋ ዉስጥ ለ35 ቀናት የዳክዬ እንቁላል እንዲቀመጥ በማድረግ እንዲፈለፈል ያደረገችዉ እናት አድናቆት እየተቸራት ይገኛል

የካሊፎርኒያ ነዋሪ የሆነችዉ እናት ከሶስት ልጆቿ ጋር በመሆን በአንድ ፓርክ ዉስጥ ጉብኝት እያደረገች ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ታዲያ የዳክዬ ጎጆ ፈራርሶ ይመለከታሉ፡፡

በጡት ማስያዣዋ ዉስጥ ለ35 ቀናት የዳክዬ እንቁላል እንዲቀመጥ በማድረግ እንዲፈለፈል ያደረገችዉ እናት አድናቆት እየተቸራት ይገኛል፡፡

በርከት ያሉ የዳክዬ እንቁላል ተሰባብሮ የነበረ ሲሆን አንዱ እንቁላል ግን ስንጥቅ ብቻ አጋጥሞታል፡፡

በዚህ ጊዜ እናት ሮዝ ከልጆቿ እንቁላሉን እንድታድነዉ ጥያቄ ይቀርብላታል፡፡

እናትም ሳታቅማማ ለ35 ቀናት እንቁላሉን በጡት ማስያዣዋ በመታቀፍ ዳክዬ እንዲፈለፈል አድርጋለች፡፡ ስትተኛ ሁሉ እንቁላሉን ታቅፋ ትተኛ እንደነበረ ተነግሯል፡፡

እንቁላሉ ለመፈልፈል በቂ ሙቀት የሚያስፈልገዉ መሆኑን ተከትሎ ይህንን እርምጃ እናት መዉሰዷን ተናግራለች፡፡

ጦማር/ዜና

ማኔ ቴቀል ፋሬስ

በአሜሪካ መዲና ክስተቱ ከተፈፀመ ዉሎ አድሮአል።።።በአጋጣሚም ከክስተቱ ከጥቂት ቀናት በኃላ ከቤተሰብ ጋራ የስፖርቱን በአል ለመታደም ወደመዲናዋ አቀናን።።።ካለፍንበት አይቀር በማለት ቤተሰብን ይዤ ነጭ ቤት ተብሎ በሚጠራዉ ወደ አሜሪካ ቤተመንግስት ደጃፍ አቅንተን ነበር።።።።ይህቺን የነፃነት እና የብሩህ ተስፋ የተጎናፀፈችን አገረ አሜሪካን ከተቀላቀልኩ አመታቶች ሳስቆጥር በዚህ በቤተመንግስት ደጃፍ እግሬን ሳስረግጥ ይህ የመጀመሪያዬ ባይሆንም ባሁኑ ግን ውስጤ ነጩ ቤት ክብር የሌለዉ ወና ባዶ ቤት መስሎ ታየኝ።።።።።ጥቁር ስለሆነ ብቻ ሳይሆን ከዛም አልፎ ባባቱ ከጎረቤት አገር ኬንያዊ: በናቱ ነጭነትን ይዞ በሃይማኖት አባቱ ሙስሌም ሆኖ: የናቱን ሃይማኖት ክርስትናን መርጦ በዉነት ይህቺን ብኩን አለምን የመሰለ የአሜሪካ ፕሬዘዳንትን የዛሬ ሰባት አመት ገደማ ስንመርጥ በኩራት እና በደስታ ነበር።።።።የነጩን ቤት ስልጣን ከተረከበ በኃላም በአሜሪካ የፖለቲካ ታሪክ ይከናወናሉ ተብለዉ ያልታሰቡትን አጀንዳዎች በከባድ ሰላማዊ ጦርነት እዉን እንዲሆኑ በማድረጉ እጅ ነስተናል።።።ሆኖም ከቀናቶች በፊት ግን የአሜሪካ ሱፕሪም ኮርት በ ግብረሰዶማውያን ላይ በወሰኑት አሳዛኝ ዉሳኔን አስታኮ ከሁለት መቶ አመት በላይ ተከብሮ በርካታ ፕሬዘዳንቶችን አሳልፎ እዚህ የደረሰዉን ቤተመንግስት እንዲረክስ አድርጎታል።።።።በግሌ ከአምላክ ትእዛዝ ዉጪ መመራትን ባልቀበለዉም።።።።የፕሬዘዳንቱ ዉሳኔ እራሱን የቻለ ሌላ ፖለቲካዊ ትርምስ እንዳለዉ ይገባኛል።።።።ነገር ግን ንብረቱ የአሜሪካ ህዝብ የሆነዉን ቤተመንግስት።።።ፕሬዘዳቶች እንዲሰሩበት እና እንዲኖሩበት ይሰጣቸዋል እንጂ በቤተመንግስቱ ላይ ደስታን ለመግለፅ በቁጥር ከሶስት ፐርሰንት ለማይበልጡት የግብረሰዶማውያንን ምልክት የሆነዉን ቀለም ማብራት በከፍተኛ ደረጃ ህዝብን መናቅ እና መድፈር ነዉ።።።።። ፕሬዘዳንት ኦባማ ለዚህም ነዉ ማኔ ቴቄል ፋሬስ ያልኮት።።።አዎ በጣም ቀለዉ ተገኝተዋል።።።።ይህን ቅለት ይዘዉ በቅድስት ኢትዮጲያ ለመሄድ ዝግጅት ላይ እንደሆኑ ይታወቃል ይህን ትርምሶን አገሪቷ አትፈልገዉም።

የሚጠቅማትን ይዘዉ ይሂዱ።
ማኔ ቴቀል ፋሬስ (ተመዝነህ ቀለህ ተገኘህ)

ዘካርያስ ጌታቸዉ