ሜርኩሪ መሰል ማዕድን እና የግንባታ ብረት በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰምቷል

ሜርኩሪ መሰል ማዕድን በሕገ-ወጥ መንገድ ከሀገር ለማስወጣት እና ግምታዊ ዋጋው 300 ሺህ ብር የሆነ ሕገ-ወጥ የግንባታ ብረት ወደ ጅግጅጋ ለማስገባት ሲሞከር በቁጥጥር ሥር መዋሉን የገቢዎች ሚኒስትር የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ የሆኑት አቶ አዲስ ይርጋ በተለይም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ተጠርጣሪ ሀሰን አህመድ ሜርኩሪ መሰል ማዕድኑን በሕገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር በፖሊስ አባላት ተይዞ የማጣራት ሥራ እየተሰራ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

በሌላ በኩል ሕገ-ወጥ የግንባታ ብረት ጭኖ ወደ ጅግጅጋ ከተማ ሊገባ የነበረ ተሸከርካሪ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

የመኪና አሽከርካሪው ለጊዜው ስላመለጠ ማህበረሰቡ ለሕግ በማቅረብ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ባለሙያው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በጨማሪም ለሚኒስቴር መ/ቤቱ በሚቀርብ ጥቆማ ኮንትሮባንድ ከተያዘ የወሮታ ክፍያ ስለሚከፈል ማህበረሰቡ ሕገ-ወጦችን በመጠቆም ተጠቃሚ እንደሚሆንም ጭምር አቶ አዲስ ጨምረው ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል፡፡

ፍሬህይወት ታደሰ