ንቁ

ሰኞ ምሽት ከ12:30 እስከ 2:00 ሳሙኤልና ዮዲት

ንቁ የሬዲዮ ፕሮግራም ፡ - በሳሙኤልና ዮዲት የስነ-ልቦና ማማከርና ስልጠና እየተዘጋጀ በተወዳጁ ጣቢያ ብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ላይ የሚቀርብ የስነ-ልቦናና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር የመዝናኛና የቁምነገር የሬዲዮ ዝግጅት ነው፡፡ ዘወትር ሰኞ ምሽት ከ12፡30 እስከ 2፡00
በ90 ደቂቃ ቆይታችን "ምስጋና" እና "የእኔ ታሪክ" የተሰኙ ዝግጅቶች ይቀርባሉ፡፡
1. ምስጋና፡ - በሬዲዮ ታሪክ የመጀመሪያውና ፋና-ወጊ የሆነ ዝግጅት ነው፡፡ በዝግጅቱ መልካምነት ከፍ ከፍ ተደርጎ ይወደሳል፤ በአስተማሪነትም ለአድማጮች ይቀርባል፡፡ እንደጠቅላላው በማህበረሰባችን ውስጥ የምስጋና ባህል እንዲዳብር ይሰራል፡፡
2. የኔ ታሪክ፡ - በስነ-ልቦና እገዛ መስጫ ማዕከላችን እገዛ ተደርጎላቸው ለውጥ ያመጡ ግለሰቦች ስነ-ልቦናዊና ማህበራዊ ግለ ታሪኮች ለአድማጮች አስተማሪ በሆነ መልኩ ይቀርቡበታል፡፡ የአድማጮች ቀጥተኛ ተሳትፎ ከባለሙያ ትንታኔ ጋር ታግዞ ይቀርባል፡፡

ዋና አዘጋጅ፡ - ሳሙኤል በጋሻው