አውቶ ሴፍቲ

ሰኞ፣ ረቡና ዓርብ ማለዳ ከ2፡30-3፡30

አውቶ ሴፍቲ በአሻንቲ አድቨርታይዝንግ እና በኦያያ መልቲ ሚዲያ ትብብር ዘወትር ሰኞ፣ ረቡና ዓርብ ማለዳ ከ2፡30-3፡30 የሚቀርብ ተወዳጅ የሬዲዮ ፕሮግራም ነው፡፡ፕሮግራሙ ከመስከረም 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ካለምንም መቆራረጥ በጉጉት በመደመጥ ላይ ይገኛል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ ግርምትን የሚጭሩ፣ በጉጉት የሚደመልጡና አስተማሪ የሆኑ ዓለም ዓቀፍና ልብ የሚነኩ ወቅታዊ የሃገር ውስጥ የአደጋ መረጃዎች፣ አስተማሪ የሆኑ የአደጋ ተጎጅ ታሪኮች፣የታዎቂ ሰዎች መልካም ተሞክሮዎች፣ የፍርድ ውሳኔ ያገኙ የአደጋ ክሶች፣ ትራፊክ ነክ ህጎችና ወቅታዊ ትራፊክ ነክ መረጃዎች አድማጭን እያሳተፉ ይቀርባሉ፡፡

አዘጋጆቹ ኢኒስፔክተር አሰፋ መዝገቡ (የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያና ከ20 ዓመት በላይ ልምድ፣ በዘርፉ የዳበረ ልምድና ግንዛቤ የማስጨበጥ ልምድ ከተሰሚነትና ተዓማኒነት ጋር) እና አሸናፊ ታደለ ( ከአ.አ.ዩኒቨርሲቲ ጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን በከፍተኛ ማእረግ የዲግሪ ምሩቅና በጋዜጠኝነት (በተለይ በሴፍቲ የሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅነት ከ10 ዓመት በላይ ልምድ) ናቸው፡፡