ጦማር/ዜና

የአቤል የመድረክ

ማቀንቀን ከጀመረ አምስት አመታትን አሳልፏል, ስሙም በመላዉ አለም በአጭር ጊዜ ዉስጥ ነዉ እንደእንዝርት መዞር የጀመረዉ,,,በአጭር ጊዜ ዉስጥ በሙዚቃ አለም እንዲህ አይነት ስኬትን ያዘለችን ምድርም እንኳን ግራ ሳይገባት አይቀርም። አዎ እማወራዉ ምንም እንኳን እትብቱ በእናት ኢትዮጰያ ባይቆረጥም: በናቱም ባባቱም ኢትዮጰያዊ ደም ያለዉን: በኛ ዘንድ ብዙም ያልተወራለትን አለም ግን እጅ እየነሳችለት ስላለዉ ድምፃዊ፣ ዘፈን ፀሃፊ እና የሬኮርድ ፕሮዲዉሰር ’አቤል ተስፋዬ ’አካ ዊኬንድ’(The Weeknd)ነዉ።

በአንዳዶቹ የሚቀጥለዉ ማይክል ጃክሰን የሚሉት ይህ ታሪካዊ ወጣት ድምፃዊ የተወለደዉ በፈረንጆቹ ካላንደር በ1990 ላይ በጥቅምት ወር ላይ ሲሆን: ቦታዉም በካናዳ በስካርብሮ በኦንትርያል ነዉ። እናትና አባቱ ከኢትዮጰያ የወጡት በፈረንጆቹ ካላንደር በ1980ዎቹ ላይ ነበር። አቤል ሲያድግ አባቱ አብሮት ስላልነበረ እናቱ ደሞ በጣም በስራ የተወጠረች ስለነበረች አቤልን ያሳደጉት አያቱ ስለነበሩ አቤል አፉን የፈታው በአማርኛ ስለነበረ አማርኛ በደንብ ያወራል።

የአቤል የመድረክ ስም ዊኬንድ የሚባል ሲሆን የዚህ ስም አመጣጥ አቤል በ17 አመቱ ላይ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በቃኝ ብሎ ከትምህርት ሲሰናበት: በዛዉ ነበር ቤቱን በሰንበት(Weekend) ላይ ለቆ ያልተመለሰዉ። በዚህም ምክንያት ነዉ የመድረክ ስሙን ዊኬንድ(Weeknd) ያለዉ። አፃፃፉን ለየት ያደረገዉ በካናዳ አገር ተመሳሳይ ስም ያላቸዉ ባንድ ስለነበረ የሱን በአንዲት ፊደል እንድትለይ ሆነ።

በፈረንጆቹ 2010–11 ላይ ነበር በቶሮንቶ ከተማ ጀርሚ ሮስ የተባለዉን ፕሮዲዉሰር አግኝቶ ወደ መጀመሪያዉ አልበሙ የገባዉ። አቤል በዚህ የፍጥነት ጎዳናዉ ላይ ስለነበረዉ ግስጋሴ ብዙ ማለት እችል ነበር አሁን ግን ቀጥታ በዚህ በአጭር የስኬት ጉዞ በእጁ የጨበጠዉን አንዳንድ ሽልማቶችን ለማየት እንሞክር።

በ2012 የዌብ ቦርን(Web born Artist)፣ ብሬኪንግ ዉዲ(Breaking Woodie)፣ የአመቱ ሶሎ አርቲስት(Sol Artist os the year)፣ የብሬክትሩ(Breakthrough) እና የአር ኤንድ ቢ(R&B) ምርጥ ቅጂ በመሆን የተሸለመ ሲሆን

በ2013 በምርጥ ቪዲዮ፣ ምርጥ አዲስ ዘፋኝ እንዲሁም በሌሎች እጩ ነበር
በ2014 የአላን ስላይት(Allan Slaight) ተሸላሚ እና የአመቱ ምርጥ አርቲስት ሆኗል

በ2015 የሴንትሪክ አዋርድ(Centric) ተሸላሚ ሲሆን አመቱ ስላላለቀ በተለያዩ አዋርዶች እጩ እንደሆነ ለማየት ችለናል።

የአቤል ትልቁ ስኬት አንድ ዘፋኝ ዘፈኖቹ በሙዚቃ ቢል ቦርድ በአንድ ጊዜ አንደኛ፣ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሲሆን በአለም የዘፋኝ ታሪክ ይህ ለመጀመሪያ ነዉ። ማንም ዘፋኝ ከነማይክል ጃክሰን ጀምሮ ይህ ዉጤት የለዉም። The Hills, Earned it, ‘Can’t Fell My Face የተባሉት ዘፎኖቹ ከአንድ እስከሶስት ቢል ቦርድን (Billboard) ተቆጣጥረዉት የነበረዉ። አሁንም በዚህን ሰአት በቢል ቦርድ ላይ ቁጥር አንድ ዘፈን
‘Can’t Fell My Face የተባለዉ የኢትዮጰያዊው አቀንቃን የአቤል ተስፋዬ አካ ዊኬንድ(The Weeknd) ነዉ።

ጋብዣለሁ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *