ጦማር/ዜና

የኦባማ ስኬት/የአፍሪቃ ጉዞ

የአሜሪካ ፓለቲካ ሂደት እጅግ ከባድ እና ዉጣ ወረድ ያለዉ ነዉ። ፖለቲካዉ በሁለት ትላልቅ ፓርቲዎች የተወጠረና ፓርቲዉን የሚመሩት ግለሰቦች ከአገራዊ አመለካከት ለፓርቲአቸዉ አድልኦ ስላላቸዉ አንድ ፕሬዘዳንት የሚፈልገዉን ሰርቶ መቀመጫዉን ለመልቀቅ በጣም አስቸጋሪ ነዉ። ፕሬዘዳንት ኦባማ ከብዙ መሰናክሎች በኃላ የሚከተሉትን በታሪክ እንዲዘገቡ አድርገዋል።
1, የቀጥታ 65 ወራቶች የኢኮኖሚ እድገት
2, የግል ስራዎች እድገት ( longest period of private sector job creation in American history)
3, ስርአጥነት ከ10.1(2009) ወደ 5.4 መዉረድ(2015)
4, ፕሬዘዳንቱ ቢሮዉን ከተረከቡ ጀምሮ የካንፓኒዎች አክስዮን እድገቱ በሬኮርድ ነዉ።( The stock market continues to set new record high)
5, የመንግስት ብሔራዊ እዳ በ2/3 መዉረድ (ከ2009 በኃላ)
6, በፕሬዘዳንቱ ጃንጥላ ስር የመንግስት ወጪ ያደገዉ በ3.3% ብቻ ነዉ። ይህ ከቀድሞዉ ፕሬዘዳንት አይዘንሃወር በኃላ የመጀመሪያዉ ነዉ።
7, የቀረጥ ክፍያ ለ95% የአሜሪካ ከፋዮች አንሶአል። ይህ በ50 አመት ታሪክ ዉስጥ የመጀመሪያዉ ነዉ
8, ኦባማ ኬር(Affordable Care Act) በሚባለዉ አማካኝነት ወደ 10ሚሊዮን የሚሆኑ ግለሰቦች የህክምና ኢንሹራስ አላቸዉ
9, በ11 አመት ታሪክ ዉስጥ አሁን በቁጥራቸዉ የሚያንሱ ወታደሮች፣ አየር ሃይሎች፣ ማሪኖች በጦርነት ቦታ ላይ ይገኛሉ
10, በፕሬዘዳንቱ ዘመን: ከምንም ጊዜ በበለጠ ወረቀት የሌላቸዉ ዜጎች ተይዘዋል: ወደመጡበት እንዲመለሱም ተደርገዋል።
11, በምንም መልኩ ሊታሰብ የማይችለዉን ኒዉክለርን በተመለከተ ከኢራን ጋራ ሰላም እንዲወርድ አድርገዋል።

ፕሬዘዳንቱ አንድ አመት ከጥቂት ወራቶች ይቀራቸዋል። አንዱ የሚቀጥለዉ አጀንዳቸዉ የአለምን አዳጋች የአየር ንብረትን በተመለከተ ይመስላል። ወደ አሁግረ አፍሪቃ አንቅተዉ ዛሬ ያባታቸዉን አገር ኬንያን ለመጎብኘት እና እናት ኢትዮጰያን ለማየት ምድረ አፍሪቃን ይረግጣሉ…እሮብ ለት በቤተመንግስታቸዉ የ(African Growth and Opportunity Act) ሲፈርሙ አፍሪቃ የሚቀጥለዉ የአለም የኢኮኖሚ ምሰሶ እንደምትሆን ተናግረዋል….ባለፈዉ ወር ፕሬዘዳንቱ ከሀጉሪቷ ጋራ ያለዉን የTrade authority ለ10 አመት ያስቀጠሉት ሲሆን… ይህ ትሬድ ወደ 350000 የሚሆኑ ስራዎችን እንደሚያቅፍ ተነግሮአል….ኢትዮጰያ ምንም እንኳን በቀድሞዉ ንጉስ በግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዘመን ከአሜሪካ መሪዎች ጋራ የነበራት ትስስር ጥሩ ቢሆንም መሬቷን ለመርገጥ የደፈረ እና የታደለ ፕሬዘዳንት ማንም አልነበረም…ይህ የፕሬዘዳንት ኦባማ ጉብኝት በኢትዮጰያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ይሆናል።

ቸር ይግጠመን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *