መደበኛ ያልሆነ

ሕይወት ፋና ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከአንድ ሴት 7 ኪሎ ግራም የሚመዝን Ovarian Cancer እጢ በኦፕራሲዮን አውጡላት

ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በሚገኘው ሕይወት ፋና ስፔሻላይዝድ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል የማህጸንና ጽንስ ህክምና ስፔሻሊስ ሐኪሞች መስከረም 30 ቀን 2011 ዓ.ም 7 ኪሎ የሚመዝን Ovarian Cancer የሴት እንቁላ ከሚያመርተው በቀዶ ጥገና በማውጣት ኦፕሬሽኑ በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ።

በስምንት አባላት የያዘው የህክምና ባለሙያዎች ለአንድ ሰአት ከሰላሳ የፈጀ የተሳካ ኦፕሬሽን ማረጋቸውን በሐረማያ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በሚገኘው ሕይወት ፋና ስፔሻላይዝድ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል የማህጸን እና ጽንስ ስፔሻሊስትና የህክምና ቡድን መሪ የሆኑት ዶክተር አሌክሳንደር መሀመድ ኢብራሂም ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋ፡፡

በአካባው የሚኖሩ እድሜያቸው በሀምሳዎቹ የሚገኙ ለስድስት ወራት በህመም ሲሰቃዩና ሆዳቸውም ከእለት ወደእለት እየጨመረ በመምጣቱ ወደ ጤና ጣቢያ ሲያመሩ ለተሸለ ህክምና  ወደ ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በሚገኘው ሕይወት ፋና ስፔሻላይዝድ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል መላካቸውን በሆስፒታሉም በተደረገላቸው ተከታታይ ህክምና ኦፕራሲዮን ማስፈለጉን ዶክተር አሌክሳንደር ለብስራት ሬድዮ ተናረዋ፡፡

ታካሚዋ የያዘቸው የካሰር አይነት የሚዛመት መሆኑንና አለመሆኑን ለማወቅ የላራቶሪ ናሙና ወደ አዲስ አበባ መላኩን ለማወቅ ችለናል፡፡

 

በትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *