መደበኛ ያልሆነ

ሴት ሰራተኞች

የህፃናት ማቆያን በከፈቱ የመንግስት ተቋማት አገልግሎት የሚሠጡ ሴት ሰራተኞች ለልጆቻቸው የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲጠቀሙ መደረጉ ተነገረ፡፡

 

የሴቶች ፤ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር የመንግስት ሰራተኛ እናቶች የህፃናት ማቆያ አገልግሎት እንዲያገኙ ባደረገዉ ጥረት አገልግሎቱ በተወሰኑ መስሪያ ቤቶች እንዲሰጥ መደረጉ ይታወሳል፡፡

ሆኖም ወደ ማቆያዉ ልጆቻቸዉን ይዘዉ ሲመጡ ከፍተኛ የትራንስፖርት ችግር ስለሚገጥማቸሁ ለከፋ እንግልት መዳረጋቸዉንም ተጠቃሚዎቹ ይናገራሉ፡፡

 

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶች ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የኮምኒኬሽን ባለሙያ አቶ መላኩ ባዩ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ችግሩን ከግምት ዉስጥ በማስገባት ሚኒስቴር መ/ቤቱ የፐብሊክ ትራንስፖርት አገልግሎት ከህፃናት ልጆቻቸዉ ጋር እንዲያገኙ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሲሰራ ቆይቷል፡፡

በዚሁ መሰረትም የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች የትረንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ባደረገዉ ትብብር ቅድመ-ሁኔታዎችን ለሚያሟሉ ሴት የመንግስት ሰራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎቱ እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡

አቶ መላኩ ለብስራት ሬድዮ እንደነገሩን የጠቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎች በሚሰሩበት መስሪያ ቤት የሕፃናት ማቆያ መቋቋሙን የሚገልጽ ደብዳቤ፡፡
የሕጻኑ/የሕጻንዋ የልደት ሰርተፍኬት ፎቶኮፒ በሚሰሩበት መ/ቤት ሰው ሃይል ከዋናው ጋር ተመሳክሮ በኃላፊ ተፈርሞ እና የመ/ቤቱ ማህተም ተደርጎበት መቅረብ ይኖርበታል፡፡

ሕጻን ይዛ የምትጓጓዘው ሴት የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኛ መረጃ ተ.ቁ ፤ ሙሉ ስም ከነአያት፤ የመኖርያ አድራሻ ፤ክፈለከተማ፤ የቤትቁጥር ፤ታክሲ ወይም አውቶቡስ የምትሳፈርበት ቦታ ልዩ ስም፤ ሞባይል ስልክ ቁጥር፤ የመ/ቤት ስምና መ/ቤት የሚገኝበት ቦታ ልዩ ስም በቅጹ ተሞልቶ በሸኝ ደብዳቤ ማህተምና ፊርማ ተደርጎበት በሰውሃብት ባለሙያዎች ለየፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች የትረንስፖርት አገልግሎት ድርጅት እንዲላክ እና ለዚህ የተዘጋጀ ልዩ መታወቂያ እንዲዘጋጅላቸው ማድረግ እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡

 

በማህሌት ካሳሁን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *