መደበኛ ያልሆነ

በአዲስ አበባ ህገ ወጥ

በአዲስ አበባ 56 በህገ ወጥ መንገድ የታተሙ ፓስፖርቶችና 1ማተሚያ ማሽን በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍከ ከተማ ወረዳ 7 በመኖሪያ ቤት ውስጥ በህገ-ወጥ መንገድ የታተሙ 56 በሴት ስም የተዘጋጁ ፓስፖርቶች፣ ማተሚያ ማሽን እና አንድ ፋቃድ የሌለው ሽጉጥ በቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡
ድርጊቱን ፈፅመዋል ተብለው የተጠጠሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በክፍለ ከተማው የአውቶቢስ ተራ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል መከላከል ፈረቃ ኃላፊ ዋና ሳጂን ይርዳው እሸቴ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡
ህገ ወጥ ፓስፖርቱና ማተሚያ ማሽኑ በቁጥጥር ስር የዋለበት ቤት  በህገ ወጥ መንገድ ለበርካታ ጊዜያት ተይዞ የቆየ ቤት መሆኑ ታውቋል።
ከዚህ በተጨማሪ 290 ሺህ ብር  በቤቱ ውስጥ መገኘቱን ዋና ሳጂን ይርዳው እሸቴ ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

 

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *