መደበኛ ያልሆነ

መነጋገሪያ ከሆኑ ጉዳዮች

የአለም አቀፍ ሚዲያዎች የፊት ገጽ መነጋገሪያ ከሆኑ ጉዳዮች ዋናው ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ሴት ርእሰ ብሔር(ፕሬዝዳንት) ጉዳይ ሆኖአል::
የአለም አቀፉ የዜና ምንጭ የሆነው አልጀዚራ ሰፊ ሽፋን ሰጥቶ ካነሳቸው ጉዳዮች ዋነኛው ኢትዮጲያ የሾመቻትን ሴትፕሬዝዳንት ጉዳይ ሆኖል፡፡ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት ውስጥ ትልቅ አስዋጾ ካላቸው እንስት መካከል ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የመጀመሪያ ሴት ፕሬዝዳንት ሆኖ መመረጣቸውን አንስቷል፡፡በተጨማሪም የኢትዮጲያ አንባሳደር ሆነው በፈረንሳይ ፣በጅቡቲ እና በሴኔጋል ማገልገላቸውን ጽፏል፡፡
ቢቢሲ በበኩሉ ትኩረት ሰጥቶ ካስቀመጠው ዜና መካከል ይሀው ሲሆን በአፍሪካ ምድር የመጀመሪያዋ ልምድ ያላት ዲፕሎማት እና የሀገር መሪ ሲል አስቀምጧል ፡፡
ዋሽንግተን በበኩሉ በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛዋ ሴት ፕሬዝዳንት በማለት የጻፈ ሲሆን ሚኒስትሮቹን ተከትሎ ሴት ፕሬዝዳንት መመረጡን ሳያደንቅ አላለፈመም ፡፡ወጣጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ወደ ስልጣን መምጣቱን ተከትሎ በሀገሪቱ ቁልፍ የሚባሉ ቦታዎችን የያዙት ሴቶች መሆናቸውን አስነብቧል፡፡
የአፍሪካ የዜና ምንጭ የሆነው አፍሪካን ኒውስ በበኩሉ ለብዙ ሀገራት አምባሳደር ሆነው ማገልገላቸውን ገልጾ በቅርቡ በኬኒያ ናይሮቢ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ጋር መወያየታቸውን ጠቅሶ ጽፏል፡፡
ፍሬህይወት ታደሰ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *