በምሥራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ከሰዴ ወረዳ ወደ ሞጣ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላሻ አውቶቡስ ተገልብጦ በ32 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደረሰ፡፡ የአካል ጉዳት ከደረሰባቸው ውስጥ የአራቱ የጉዳት መጠን ከፍተኛ ነው፤ ለሁሉም ተጎጂዎችም በሞጣ ሆስፒታል የሕክምና ዕርዳታ እየተደረገላቸው ነው፡፡ አደጋው ትናንት ከቀኑ 11፡00 በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ አዲስ ዘመን ቀበሌ ነው የደረሰው፡፡ መኪናው ከልክ በላይ ተሳፋሪዎች የነበሩበት ሲሆን በመኪናው ተሳፍረው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች አሽከርካሪውን ጨምሮ 32 እንደሆኑ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ኢንስፔክተር ጎበዜ ይርሳው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡
ሳምራዊት ስዩምበምሥራቅ ጎጃም ዞን በመኪና አደጋ 32 ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ፡፡ በምሥራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ከሰዴ ወረዳ ወደ ሞጣ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላሻ አውቶቡስ ተገልብጦ በ32 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደረሰ፡፡ የአካል ጉዳት ከደረሰባቸው ውስጥ የአራቱ የጉዳት መጠን ከፍተኛ ነው፤ ለሁሉም ተጎጂዎችም በሞጣ ሆስፒታል የሕክምና ዕርዳታ እየተደረገላቸው ነው፡፡ አደጋው ትናንት ከቀኑ 11፡00 በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ አዲስ ዘመን ቀበሌ ነው የደረሰው፡፡ መኪናው ከልክ በላይ ተሳፋሪዎች የነበሩበት ሲሆን በመኪናው ተሳፍረው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች አሽከርካሪውን ጨምሮ 32 እንደሆኑ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ኢንስፔክተር ጎበዜ ይርሳው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡
ሳምራዊት ስዩም