መደበኛ ያልሆነ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ወ/ሮ ኤፍራሂ አሊን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አድርጎ ሾሟል፡፡

ወይዘሮ ኤፍራሂ አሊ ከጥቅምት 13 /2011 ዓ.ም ጀምሮ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን የኤጀንሲው የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዱልባሲጥ አህመድ በተለይም ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል፡፡

በተያያዘ ዜና በሰላም ሚኒስቴር ሚንስትር  ሙፈሪያት ካሚል የሚመራው የልኡካን ቡድን በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) በመገኘት በትናንትናው እለት ጉብኝት አድርጓል፡፡
በኤጀንሲው ጉብኝት ያደረጉት ሚኒስትሯን ጨምሮ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታዎች አቶ ዘይኑ ጀማል እና አቶ ከፍያለው ተፈራ ከኢመደኤ አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን አቶ ተስፋዬ አለም ተናግረዋል፡፡
‹‹አሁን ባለንበት ዘመን ሃገራት የሳይበር ደህንነታቸውን ካላስጠበቁ ሰላምን ማስጠበቅ ከባድ እንደሚሆንባቸው ሚኒስትሯ አስምረውበታል፡፡››
በውይይቱ ወቅትም ኤጀንሲው ራዕዩን መሰረት በማድረግ የተሻለ ስራዎችን መስራት እንዲችል እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆን ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ሳይበር ምህዳሩን በመጠቀም ሰላማችንን ሊያደፈርሱ የሚችሉ ነገሮችን መለየት እና መከላከል በሚችል መልኩ የበለጠ የማዘመን ተግባር እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

ተቋሙ በአብዛኛው በወጣቶች የተገነባ በመሆኑ በተሻለ አቅም አዳዲስ አሰራሮችን በቀላሉ የሚለምድ እና በብቃት መፈጸም የሚችል መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህነንት ኤጀንሲ አዲስ ለተቋቋመው የሰላም ሚኒስቴር ተጠሪ ከሆኑ ተቋማት አንዱ መሆኑንም አቶ አብዱልባሲጥ ጨምረው ለብስራት ራዲዮ ተናግዋል፡፡

                                                                                                    ሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *