መደበኛ ያልሆነ

በኦሮሚያ ክልል በትራፊክ አደጋ የ31 ሰው ሕይወት አለፈ፡፡

በኦሮሚያ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሰው የትራፊክ አደጋ የ31 ሰው ሕይወት አለፈ፡፡
ከጥቅምት 12 እስከ ጥቅምት 18 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ በደረሰው የትራፊክ አደጋ የ31 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 40 ሠዎች ላይ ከባድ፣29 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት እንዲሁም 20 የንብረት አደጋ አጋጥሟል፡፡
አደጋዎቹ በምስራቅ ሸዋ ዞን ሎሜ ወረዳ፣በቦረና ዞን ሞያሌ ወረዳ፣በምዕራብ አርሲ ሻሸመኔ እና ዶዶላ አርሲ ነገሌ ከተማ ፣በምስራቅ ሀረርጌ ሜታ እና አወዳይ ወረዳ፣በሰሜን ሸዋ ውጫሌ ወረዳ ፣በምዕራብ ሀረርጌና ጤለም ወለጋ ፣በሱሉልታ እና ወልመራ ወረዳዎች የደረሱ ናቸው፡፡
የአደጋው ሁኔታ ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር የጨመረ ሲሆን የአደጋዎቹ መንስኤ ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር እንዲሁም በሞተር ሳይክል አማካኝነት የሚሰጥ የትራንስፖርት ግልጋሎት እንደሆነ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኮማንደር ደረጀ ፈጠነ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡
በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *