መደበኛ ያልሆነ

ህገ ወጥ የጎዳና ነጋዴዎች

ከ 4ሺ በላይ ህገ ወጥ የጎዳና ነጋዴዎችን ህጋዊ የመሸጫ ቦታ ሊሰጣቸው እንደሆነ ተነገረ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ የመጣውን የጎዳና ላይ ንግድ ለማስቀረት የሚያስችል ስርዓት እየዘረጋ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል ፡፡
የጎዳና ላይ ነጋዴዎችን በአንድ አሰባስቦ በህጋዊ ስርዓት ውስጥ እንዲነግዱ ለማድረግ የሚያስችለው ቀዳሚ ተግባር በነገው እለት እንደሚከናወን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ በላይ ወልደሰንበት በተለይም ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡
ነጋዴዎቹ ቦታው የሚሰጣቸው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቦሌ እና የካ ክ/ከተማ ሲሆኑ የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ቦታው ላይ ተገኝተው ርክክቡን እንደሚያደርጎ ተገልጿል፡፡
በቀጣይም ቦታውን የተረከቡት ነጋዴችን ለመከታተል እና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ንግድ ቢሮው ከደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ፤ከአዲስ አበባ ፖሊስ እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ አቶ በላይነህ ወልደሰንበት ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል ፡፡
ህጋዊ ባልሆነ መንገድ የሚነግዱ የጎዳና ላይ ነጋዴዎች እስከ ጥቅምት ሰላሳ የምዝገባ ሂደቱን ማከናወን እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡
ናትናኤል ሀብታሙ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *