መደበኛ ያልሆነ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአዲሱ መዋቅር መሰረት አምስት ቋሚ ተጠሪዎችን ሾመ፡፡

የቋሚ ተጠሪነት (Permanent Secretary) ሹመት የተሰጣቸው አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ፣ አምባሳደር ማህሌት ኃይሉ፣ አምባሳደር ዶ/ር ቦጋለ ቶሎሳ፣ አምባሳደር ነጋ ፀጋዬ እና አምባሳደር ደዋኖ ከድር ናቸው፡፡

ሹመት የተሰጣቸው አምባሳደር ወይንሸት በሲዊዲን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እንዲሁም በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ነበሩ፡፡

አምባሳደር ማህሌት ኃይሉ ደግሞ በኒውዮርክ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቋሚ መልዕክተኛ ጽ/ቤት ምክትል የሚስዮን መሪ በመሆን አገልግለዋል፡፡

አምባሳደር ወይንሽት ታደሰ የአፍሪካ እና የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ጉዳዮች ቋሚ ተጠሪ፣ አምባሰዳር ማህሌት ኃይሉ የአውሮፓ፣ የአሜሪካ፣ የኤዥያ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ቋሚ ተጠሪ፣ አምባሳደር በጋለ ቶሎሳ የዳያስፖራ እና ቆንስላ ጎዳዮች ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ነጋ ፀጋዬ የኃብት ማኔጅመንትና አገልግሎት ቋሚ ተጠሪ፣ አምባሳደር ደዋኖ ከድር ደግሞ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ቋሚ ተጠሪ ሆነዋል፡፡

ቋሚ ተጠሪዎች የመስሪያ ቤቱን የዕለት ተዕለት ስራ የመከታተልና ውሳኔ የማሳለፍ ሃላፊነት የሚኖራቸው ሲሆን በተለያዩ አገሮች በስፋት ይሰራበታል፡፡ የመስሪያ ቤቱን ተቋማዊ ትውስታ ለማስቀጠልም ይረዳል ተብሎ ታምኖበታል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት ለብስራት ሬድዮ በላው መግለጫ መሰረት በቀጣይም የዳይሬክተር ጀኔራሎች እና ሌሎች የሃላፊነት እርከኖች ድልድል ይፋ ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *