መደበኛ ያልሆነ

ከሰኔ 16ቱ የቦንብ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ…

ከሰኔ16ቱ የቦንብ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ የመጨረሻ የክስ መመስረቻ ጊዜ መፈቀዱ ተሰምቷል ከሰኔ 16ቱ የቦንብ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩት አቶ ተስፋዬ ዑርጌ በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተረኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ መቅረባቸውን የጠቅላይ አቃቢ ህግ የህዝብ ግንኙነት የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱሉ ለብስራት ሬድዮ ገልጸዋል፡፡
የፌዴራል መርማሪ ፖሊስ በተለያየ ጊዜ በተጠርጣሪው ላይ ያጠናቀራቸውን መረጃዎች ለፌዴራል ዐቃቤ ህግ ባለፈው የጊዜ ቀጠሮ አጠናቆ መስጠቱ ይታወሳል፡፡
ሆኖም ግን የፌዴራል ዐቃቤ ህግ ክስ ለመመስረት በተሰጠው ጊዜ ውስጥ መዝገቡ ስላልተጠናቀቀ 12 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ እንደሚያስፈልገው ለችሎቱ አመልክቷል፡፡ የግራ ቀኙን ክርክር የተመለከተው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተረኛ ወንጀል ችሎትም ዛሬ በዋለው ችሎት የ10 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ለህዳር 7 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ
መስጠቱን የጠቅላይ አቃቢ ህግ የህዝብ ግንኙነት የኮሚዩኒኬሽን ጉዳች ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱሉ በተለይም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *