መደበኛ ያልሆነ

“ኢትዮጵያ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግ እየሰራች ነው፡፡ ”

“ኢትዮጵያ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግ እየሰራች ነው፡፡ ”ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መንግስት በኢትዮጵያ የምጣኔ ሃብት ግንባታ ሂደት ውስጥ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግ የሰጠውን ትኩረት በሚመለከት በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ገለጻ እያቀረቡ ነው፡፡

 

በኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መከናወናቸውን የጠቀሱት  ፕሬዝዳንቷ በአገሪቱ ተገንብተው የተጠናቀቁና በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በማሳያነት ጠቅሰዋል፡፡

 

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት ለብስራት ሬድዮ በላከው መግለጫ መሰረት መንግስት ወጣቶችን በ50 ዩኒቨርሲቲዎችና በተለያዩ የሙያና ቴክኒክ ተቋማት በማሰልጠን ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆነ የሰው ሃይል ለማፍራት እየሰራ መሆኑን  ፕሬዝዳንቷ ገልጸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *