የአፍሪካ ህብረት አስቸኳይ ጉባኤ ከህዳር 8-9 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉባኤው የተሳካ እንዲሆን ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ዛሬ ለሚዲያዎች በሰጡት መደበኛ ጋዜጣዊ መግለጫ ኢትዮጵያ 11ኛው የአፍሪካ ህብረት አስቸኳይ ጉባኤን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ ከህዳር 5-6 ቀን 2011 ዓ.ም ፣ ከህዳር 8-9 ቀን 2011 ዓ.ም ደግሞ በመሪዎች ደረጃ የምታስተናግድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ቃል አቀባዩ፣ የጉባኤው አጀንዳ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ማሻሻያ (Reform) የሚመለከት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
በጉባኤው ላይ የ45 አገራት መሪዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃልም ብለዋል ፡፡
አቶ መለስ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰብሳቢነት በአገር አቀፍ ደረጃ ጉባኤውን ለማዘጋጀት 30 መ/ቤቶች ያሉበት ብሔራዊ ኮሚቴ ፣ 13 መ/ቤቶችን ያካተተ ብሔራዊ የኤርፖርት ኮሚቴ እንዲሁም ሌሎች የውጭ ጉዳይ ንዑስ ኮሚቴዎች
ዝግጅት እያደረጉ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡
ማህሌት ካሳሁን