የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታዎች ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ እና ዶ/ር አክሊሉ ኃይለሚካኤል በቤይሩት የሚገኙና በተለያዩ ሁኔታዎች እንግልት የደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን ዜጎች ጊዜያዊ መጠለያን ጎብኝተዋል።
በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲዎች እና ቆንስል ጄነራል ጽ/ቤት የስራ ሃላፊዎች ጋር በመሆን በቤይሩት በሚገኘው ጊዜያዊ መጠለያ ካሉ ኢትዮጵያውያን ጋር ለአንድ ቀን የቆየ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይታቸውም ህጋዊ በሆነ መንገድ በመጓዝ ዜጎችን ከተለያዩ እንግልት መታደግ እንደሚገባ ተወስቷል።
ጊዜያዊ መጠለያው ከ70 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ከለላ በመስጠት አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል።
የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት ለብስራት ሬድዮ በላከው መግለጫ መሰረት ኤምባሲውም ከቤይሩት ኢትዮጵያውያን ማህበር ጋር በመሆን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እየሰራ ነው።
ስምኦን ደረጄ