መደበኛ ያልሆነ

66ኛው የኢጋድ አስቸኳይ የሚኒስትሮች ስብሰባ ይካሄዳል

66ኛው የምስራቅ አፍሪካ በይነ-መንግስታት ድርጅት (IGAD) አስቸኳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ነገ (ሕዳር 7 ቀን 2011 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

አስቸኳይ ስብሰባው የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ በአዲስ አበባ የተፈራረሙትን የሰላም ስምምነት አፈጻጸም በሚመለከትና ባለው አጠቃላይ የሰላም ሁኔታ ላይ ይመክራል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት ለብስራት ሬድዮ በላከው መግለጫ መሰረት የኢጋድ ድርጅታዊ መዋቅርን ማጠናከር በሚመለከት ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *