መደበኛ ያልሆነ

ኢትዮጵያና ሱዳን በጉምሩክ መስክ እንደሚተባበሩ ገለፁ

በኢትዮጵያና ሱዳን መሀከል ህጋዊ ንግድ ለማበረታታት የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴን ለመግታት በጉምሩክ ዘርፍ ያለው ትብብር መጠናከር እንዳለበት ተገለፀ፡፡

በሱዳን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳዳር ሽፈራው ጃርሶ ከአገሪቱ የጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል በሺር አልታሂር ጋር ተወያይተዋል፡፡

ብስራት ሬድዮ ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት በተላከለት መረጃ መሰረት ዕርምጃው በንግድና በጉምሩክ አገልግሎት ዙሪያ የሚያጋጥሙ እንቅፋቶችን ለመፍታት እንዲሚረዳ አስረድተዋል፡፡

አምባሳደር ሽፈራው በኢትዮጵያና ሱዳን መሀከል የተፈረመው የልዩ ንግድ ስምምነት በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ አንዲሆንም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የሱዳን ጉምሩክ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል አልታሂር በበኩላቸው ህጋዊ ያልሆነ ንግድ እና የጦር መሳሪያ ዝውውርን በጋር መከላከል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *