መደበኛ ያልሆነ

በህገ ወጥ መልኩ ወደ ጅማ ሲጓጓዝ የነበረ 530 ጄሪካን የምግብ ዘይት በቁጥጥር ስር ዋለ

የታርጋ ቁጥሩ ኮድ-3- 32654 አይሱዙ ተሸከርካሪ 530 ጄሪካን ባለ 5 ሊትር የምግብ ዘይት በህገ ወጥ መንገድ በመጫን ጭነቱን ለመደበቅ ከላዩ 120 የመኪና ጎማ ጭኖ ከአዲስ አበባ ወደ ጅማ በመጓዝ ላይ ሳለ በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉን በሰበታ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊና ምክትል ኮማንደር አደም ሃሰን በተለይም ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ህዳር 19 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰአት በሰበታ ከተማ ቀበሌ 07 ልዩ ቦታው ጎሚስታ አካባቢ ተከሳሽ አዲሱ ዳዲ የተባለው ግለሰብ ተሸከርካሪውን ይዞ ለማምለጥ ጥረት ቢያደርግም ህብረተሰቡ ባደረሰው ጥቆማ መሰረት ፖሊስ ተከታትሎ በቁጥጥር ስር ማዋል ችሏል፡፡

በዚሁ መሰረት ተከሳሹን እና ጭነቱን በሰበታ ከተማ ክፍለ ከተማ 1 ፖሊስ ጣቢያ ከገባ በኋላ የምርመራ መዝገቡ ተጣርቶ ሲጠናቀቅ ጉዳዩ ወደ ሰበታ ፍርድ ቤት ተልኳል፡፡

አቃቤ ህግ በመሰረተበት ክስ መሰረት ተከሳሹ ፍርድ ቤት ቀርቦ ጥፋተኝነቱ ከተረጋገጠ በኋላ ህዳር 20 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ 10 ሺህ ብር ቅጣት ንብረቱ ለመንገስትገቢ እንዲሆን ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን አስተላልፏል፡፡

 

ሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *