የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ክልላዊ እና ሌሎች ድርጅቶች በጋራ በመሆን በኒውዮርክ በተደረገ ጠቅላላ ጉባኤ፣ የተመድ እና አፍሪካ ህብረት ስትራቴጂካዊ አጋርነት እንዲጠናከር ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ላደረጉት አስተዋጽኦ ኢትዮጵያ አድናቆቷን ገልጻለች፡፡
በየጊዜው የሚደረጉ የመረጃ ልውውጦች እና ምክክሮችን ጨምሮ በጋራ እየተሰሩ ባሉ በርካታ ጉዳዮች ላይ ኢትዮጵያ አድናቆት ያላት መሆኑ በጉባኤው ተጠቅሷል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት ለብስራት ሬድዮ በላከው መግለጫ መሰረት፡-በአፍሪካ ህብረት ለሚመራው የሰላም ትብብር ትግበራ፣ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ላይ የበለጠ መሻሻል እንዲኖር ኢትዮጵያ ጥሪ አቅርባለች፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ክልላዊ እና ሌሎች ድርጅቶች በጋራ በመሆን በኒውዮርክ በተደረገ ጠቅላላ ጉባኤ፣ የተመድ እና አፍሪካ ህብረት ስትራቴጂካዊ አጋርነት እንዲጠናከር ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ላደረጉት አስተዋጽኦ ኢትዮጵያ አድናቆቷን ገልጻለች፡፡
በየጊዜው የሚደረጉ የመረጃ ልውውጦች እና ምክክሮችን ጨምሮ በጋራ እየተሰሩ ባሉ በርካታ ጉዳዮች ላይ ኢትዮጵያ አድናቆት ያላት መሆኑ በጉባኤው ተጠቅሷል፡፡
በአፍሪካ ህብረት ለሚመራው የሰላም ትብብር ትግበራ፣ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ላይ የበለጠ መሻሻል እንዲኖር ኢትዮጵያ ጥሪ አቅርባለች፡፡
ስምኦን ደረጄ