መቀመጫውን አዲስ አበባ ባደረገው የደህንነት ጥናት ኢኒስቲትዮት የተዘጋጀውን ስብሰባ በንግግር የከፈቱት የተቋሙ ዳይሬክተር ዶ/ር ሮባ ሽራም ናቸው፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት ለብስራት ሬድዮ በላከው መግለጫ፡- በአፍሪካ የሚከሰቱ የሰላም እና ደህንነት ፈተና ለመፍታት የተቀናጀ እና ፈጠራ የታከለበት እርምጃ መውሰድ እንደሚገባም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
የአይ.ኤስ.ኤስ አመራር ቦርድ ፕሬዝዳንት ሰኢድ ጂኔት በበኩላቸው በአህጉራቱ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመቅረፍ በአፍሪካ ህብረት እና ክፍለ አህጉራዊ ድርጅቶች መሀከል የተቀናጀ ጥረት ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡ተሳታፊዎችም በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ፈጣን ለውጥ አድንቀዋል፡፡
ስምኦን ደረጄ