በ2010 በኢትዮጲያ ዓለም አቀፍ የኦሎምፒክ ጫወታዎችን ማስኬድ የሚያስችሉ 11 እስቴድየሞች በመገንባት እና በመታደስ ላይ መሆናቸውን የስፖርት ኮሚሽን የኮሚንኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ናስር ለገሰ በተለይም ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል፡፡
እየተገነቡ ያሉት የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች ከቻይና ተቋራጭ ኢንጅነሪንግ ጋር በጋራ በመሆን እየተገነቡ ይገኛሉ፡፡
የስቴድየም ግምባታዎቹ የመወዳደሪያ አቅምን ማሻሻል የሚችሉ በስፖርቱ ላይም ጥሩ ለውጥ ለማምጣትም የጎላ ጥቅም አላቸው ተብሏል፡፡
በተጨማሪም የተሻለ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎችን በመገንባት እና ስፖርቱን ለማገዝ መንግስት ብቻ ሳይሆን የግሉ ባለሀብቶች የበኩላቸውን ተሳትፎ ማድረግ አለባቸው ሲሉ አቶ ናስር ጨምረው ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል፡፡
ሳምራዊት ብርሀኑ