ብስራት ሬድዮ ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት በተላከለት መረጃ መሰረት የጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢማኑኤላ ዲልሪ ከነገ ጀምሮ ለአራት ቀናት በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡
በጉብኝታቸው ወቅት ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የፋይናንስ ሚኒስቴር፣ የንግድ ሚኒስቴርና ግብርና ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች ጋራ ተገናኝተው ይወያያሉ፡፡
በአዲስ አበባ የሚገኘውን የጣሊያን የባህል ማዕከልና የደንቦስኮ የወጣቶች ማዕከልና ትምህርት ቤትን እንዲሁም በጣሊያን መንግስት የሚደገፈውን የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ተቋምን እንደሚጎበኙም ታውቋል፡፡
በኢትዮጵያ ከሚኖሩ የጣሊያን ማህበረሰብና በኢትዮጲያ ኢንቨስት ካደረጉ የጣሊያን ባለሀብቶች ጋር ተገናኝተው እንዲወያዩ መርሃ ግብር ተይዞላቸዋል፡፡
በቅርቡ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ በኢትዮጲያ ተገኝተው ይፋዊ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
ስምኦን ደረጄ