መደበኛ ያልሆነ

91.8 ሚሊዮን ብር ፈሰስ የተደረገበት ፣ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድኃኒቶች እና ኬሚካሎችን የሚያስወግደው መሳሪያ አገልግሎት ሊጀምር ነ ው

የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸውና በተለያዩ ምክንያቶች ጥቅም ላይ የማይውሉ መድኃኒቶችን
እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ኬሚካሎችን በዘመናዊ መንገድ ማስወገድ የሚያስችል መሳሪያ
አገልግሎት መስጠት ሊጀምር መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማን
በተለይም ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል፡ ፡
መሳሪያው በሰዓት 1000 ኪ.ግ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድሀኒቶችን
የሚያስወግድ ነው።
በ91.8 ሚሊዮን ብር ወጪ ተተክሎ የ ትግበራ ሙከራው የ ተጠና ቀቀ ሲሆን በመጪዎቹ ሶ ስት
ሳምንታት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ አገ ልግሎት መስጠት እን ደሚጀምር ታውቋል፡ ፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ በ3.5 ቢሊዮን ብር በመገንባትና በመተከል ላይ ያሉት ሰባት
ማሽኖችም በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ ሚኒስትሩ ጨምረው
ለብስራት ራዲዮ ገልጸዋል፡ ፡
ፍሬህይወት ታደሰ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *