በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከስነርጂ ሀበሻ ፊልም፣ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጅ ጋር ‹‹ቴክኖቬሽን ኢትዮጰያ›› በተሰኘ ፕሮግራም ሴቶች በተለያዩ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ በጋራ እየተሰራ ነው ሲሉ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ገብረጊዮርጊስ አሰፋ በተለይም ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል፡፡
የሴቶች ችግር ፈቺ የሞባይል መተግበሪያዎችን በመስራት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማድረግ እና በሶፍት ዌር ዲቨሎፐመት ላይ ያላቸውን አቅም ለማዳበር ፕሮግራሙ እንደሚያግዝ ተገልጿል፡፡
ፕሮግራሙን አጠናክሮ ለማስቀጠል እና ወደ ክልሎች በማውረድ በደቡብ እና በኦሮሚያ ክልሎች ለማስጀመር አቶ ጀማል በከር እና የሲነርጂ ሀበሻ ፊልም ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሀላፊ ዶ/ር ሞገስ ታፈሰ የመግባቢያ ስምምነተ ተፈራርመዋል ሲሉ ጨምረው ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል፡፡
ሳምራዊት ብርሀኑ