መደበኛ ያልሆነ

ቱርክ የኢትዮጵያን ልማት እንደምትደግፍ ገለጸች

የቱርክ የትብብር ኤጀንሲ ፕሬዘዳንት በቱርክ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልክተኛና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ግርማ ተመስገን ጋር ባደረጉት ውይይት ኤጄንሲው በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ዘላቂ ልማት እንደሚደግፍ ገልጸዋል፡፡

ኤጄንሲው በኢትዮጵያ ለሚገኘው የአል-ነጋሺ መስጅድ እድሳት እንዲሁም በሐረር ከተማ የሚገኘውን የኦቶማን ቆንስላ ጽ/ቤት በአዲስ መልክ እንዲታደስ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ ያለውን አጠቃላይ ልማት አድንቀው ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።

አምባሳደር ግርማ ተመስገን በበኩላቸው ኤጀንሲው ለኢትዮጵያ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አድንቀው፤ ድጋፉን በሌሎች የዘላቂ ልማት ግቦች መሳካት ላይም አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

በተጨማሪም አምባሳደሩ ከቱርክ ታዋቂው የፖለቲካና ኢኮኖሚ ጥናት ማዕከል ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ሙቲን አታማን ጋር በአፍሪካ ቀንድና በቀይ ባህር አካባቢ እየጨመረ ሰለመጣው ጅኦፖለቲካል አንቅስቃሴ ላይ ተወያይተዋል።

ብስራት ሬድዮ ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት በተላከለት መረጃ መሰረት በቀጣይም በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አምባሳደር ግርማ ተመስገን ከጅቡቲ አቻቸው ጋር በዛሬው ዕለት በሁለትዮሽ ጉዳዩች ዙሪያ፣ በኢንቨስትመንትና ንግድ ላይ ያተኮረ ውይይት በአንካራ አድርገዋል፡፡

 

ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *