መደበኛ ያልሆነ

በህገ ወጥ መልኩ በኮንትሮባንድ ሲዘዋወሩ ነበሩ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ግምታዊ ዋጋው 500 ሺ ብር የሆነ የተለያየ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ጭኖ ሲንቀሳቀስ የነበረ ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር መዋሉን በገቢዎች ሚኒስቴር የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አዲስ ይርጋ በተለይም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ተሸከርካሪው በህገ ወጥ መንገድ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ጭኖ ከጅግጅጋ ወደ ሐረር በመሄድ ላይ እያለ በፌደራል ፖሊስ አባላት አማካኝነት በትናንትናው እለት ከለሊቱ 9 ሰዓት ላይ እንደተያዘ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ህብረተሰቡ ይህንን መሰል ህገ-ወጥ ተግባሮችን ለመከላከል ጥቋማ እና ድጋፍ ሊሰጥ ይገባል ሲሉ አቶ አዲስ ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ሳምራዊት ብርሀኑ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *