መደበኛ ያልሆነ

በኦሮሚያ በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ የፀጥታ ችግር እንዳለ ተሰማ

የፀጥታ ችግሩ ያለባቸው አካባቢዎች በኦሮሚያ በምእራብ ጉጂ ዞን ፣ በምዕራብ ፣ ምስራቅ ፣ ውሩ ወድሮ እና ቀለም ወለጋ መሆናቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ሐላፊ ኮማንደር ደረጄ ፈጠነ በተለይም ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡
በአካባቢዎቹ ላይ የተለያዩ ችግሮች በመፈጠራቸው የትምህርት መቆራረጥ እንዲሁም የአካባቢው ህብረተሰብ በነፃነትና በሰላማዊ ሁኔታ እንዳይንቀሳቀሱ ሆነዋል ተብሏል፡፡
እንደነዚህ አይነት ችግሮች ለሰላም ፀር የሆኑ ብሎም የማህበረሰቡ የአኗኗር ሁኔታ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ የሚያሳድሩ በመሆናቸው ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል፡፡
ይህንን ችግር ለመፍታት መንግስት በዚህ 3ት ወር ውስጥ ውይይት እያደረገ መሆኑን እና አንፃራዊ ሰላም መታየቱን አቶ ደረጄ ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ቃልኪዳን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *