የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከአየርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድካራ ጋር ተወያይተዋል።
ብስራት ሬድዮ ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት በተላከለት መረጃ መሰረት መሪዎቹ በውይይታቸው የሁለትዮሽ ግንኙነት ማሳደግ በሚቻልባቸው እና በክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አካሂደዋል።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እየተከናወነ ያለውን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ አየርላንድ እንደምትደግፍ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይቱ አረጋግጠዋል።
አየርላንድ የኢትዮጵያን ልማት ከሚደግፉ ሃገራት መካከል አንዷ ስትሆን፥ ሃገሪቱ በአየርላንድ የልማት ተራድኦ አይሪሽ ኤድ አማካኝነት ለገጠር ልማት፣ ለጤና አገልግሎት እና ለተለያዩ ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ድጋፍ ታደርጋለች።
የአየርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ትናንት ማለዳ ኢትዮጵያ የገቡ ሲሆን፣ በቆይታቸውም ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ይወያያሉ።
ስምኦን ደረጄ