መደበኛ ያልሆነ

በመንግስት የሚጠበቅን ደን የጨፈጨፉ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

ድርጊቱ የተፈፀመው በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሀርጌ ዞን ከረፍ ጨሌ ወረዳ ጉዲና ሙለታ ቀበሌ ነው፡፡ተከሳሾች በቁጥር ስድስት ሲሆኑ አንደኛ ተከሳሽ አብዲ መሀመድ 2ተኛ አብደላ ኩፌ፣ 3ተኛ አደም አብዱርሀማን፣ 4ተኛ ሽፈራው አብርሀም፣5ተኛ ኩፌ መሀመድ እና አብሀም መሀመድ የተባሉ ግለሰቦች ናቸው፡፡ለዓመታት በመንግስት የሚጠበቀውን ደን በተለያዩ ጊዜያት ጨፍጭፈው በመውሰድ ለተለያዩ ግልጋሎቶች እንዲውል በማድረግ ገበያ ላይ ያቀርባሉ፡፡የአካባቢው ህብረተሰብ ድርጊቱን በተደጋጋሚ በማየታቸው ለፖሊስ ያመለክታሉ፡፡ፖሊስም ድርጊቱን በማጣራት ተከሳሾቹን አፈላልጎ በቁጥጥር ስር ያውላል፡፡

የክስ መዝገቡ ተጣርቶ ለኩፉ ጨሌ ወረዳ ፍ/ቤት ይላካል፡፡ ፍ/ቤቱም ተከሳሾቹ እያንዳንዳቸው ጥፈተኛ ሆነው ስላገኛቸው አንደኛ ተከሳሽ በ6ዓመት ከ3ወር እስራት እና በ7ሺ ብር፣ ሁለተኛ ተከሳሽ በ6ዓመት ከ3ወር እና በ4ሺ ብር፣ ሦስተኛ ተከሳሽ በ6ዓመት እና በ4ሺ ብር፣ አራተኛ ተከሳሽ በ5 ዓመት እና በ1ሺ ብር ፣አምስተኛ እና ስድስተኛ ተከሳሾች በ5ዓመት እስራት እና በ8መቶ ብር እንዲቀጡ መወሰኑን የኦሮሚያ ክልል የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኮማንደር ደረጄ ፈጠነ በተለይም ለብስራ ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *