የቀድሞ የአሜሪካ የቤቶችና የከተማ ልማት ፀሀፊ የ44 ዓመቱ ካስትሮ ዲሞክራቶችን በመወከል የትራምፕ ዋንኛ ተቀናቃኝ እንደሚሆኑ ታውቋል፡፡
በትውልድ ስፍራቸው ቴክሳስ ፤ ሳን አንቶኒዮ ካስትሮ እንደተናገሩት የትራምፕ አስተዳደር አሜሪካን ወደ ቀውስ ከቷል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በቅስቀሳው ላይ የተገኙት የቴክሳስ የዲሞክራቶች ተወካይ እና የጁሊያን ካስትሮ ወንድም ጆአኪን ካስትሮ በደጋፊዎች እገዛ እና ትብብር የተሻለ እጩ እና የተሻለ መሪ አሜሪካ ይኖራታል ሲሉም ተደምጠዋል፡፡
ካስትሮ በኦባማ አስተዳደር ከፍተኛ ስልጣን የነበራቸው ሲሆን በጤናው ረገድ አመርቂ የስራ ውጤት ማስመዝገባቸውም ይታወሳል፡፡
የሳን አንቶኒዮ ከተማ ከንቲባ በነበሩበት ጊዜ ደካማ የስራ አፈፃፀም ነበራቸው ሲሉ የሪፓብሊካኑ ብሄራዊ ኮሚቴ ቃል አቀባይ ሚካኤል ኸርንስ ተናግረዋል፡፡
በ2020 ምርጫ ካሸነፉ የመጀመሪያው የላቲን የዘር ሀረግ ያላቸው መሪ ይሆናሉ፡፡
ሚኪያስ ፀጋዬ