መደበኛ ያልሆነ

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ወደ ስራ የገባው የምህረት አዋጅ በትናንትናው እለት ተጠናቋል

ከአሁን ቀደም በሀገሪቱ በነበረው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ተሳታፊ የነበሩ እና በሽብርተኝነት የተፈረጁ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የታሰበው የምህረት አዋጅ ከሃምሌ 13 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ መዋሉ ይታወሳል፡፡በመሆኑም በሀገሪቱ ያለውን ለውጥ ለማጠናከር እና ዘለቄታዊ መፍትሄ እንዲሆን ታስቦበት ከውሳኔ እንደተደረሰ በፌደራል ይቅርታ ቦርድ ፅ/ቤት ዋና ኃላፊ አቶ ዘለቀ ዳላኖ ከዚህ ቀደም ለብስራት ሬድዮ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

በዚህም መሰረት በፌደራል ደረጃ 800 በአጠቃላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ 13 ሺህ 122 ያክል ዜጎች የምህረት ተጠቃሚ ሁነዋል፡፡የምህረት አዋጁን ተደራሽ ከማድረግ አንፃር ከዘጠኙም ክልሎች ጋር በቅንጅት ተሰርቷል፡፡ ኑሯቸውን ከሀገር ውጪ ያደረጉትን ተጠቃሚ ለማድረግም በተቋሙ ድህረ ገፅ በኩል ማስተናገድ መቻሉን አቶ ዘለቀ ተናግረዋል፡፡

ለስድስት ወራት የቆየው የምህረት አዋጅ በትናንትናው እለት መጠናቀቁን የፌድራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ የህዝብ ግንኙነት ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱኑ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ፍሬህይወት ታደሰ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *